
ሰበር ዜና!!! ቴዲ አፍሮ 1,000.000.00 ብር ለቦረና #ዓድዋ_127_ለቦረና የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር ለግሷል። የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል። በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መሪነት መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዓድዋ ላይ ወራሪን ድባቅ በመምታቱ በዓለም የነጻነት መድብል ውስጥ ኢትዮጵያ የታሪክ ማማ ላይ መስፈር ችላለች። 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ኹሉ በትብብር እና በአንድነት በመቆም የአያቶቻችንን አደራ መጠበቅ ይገባናል። በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል እንደ ወትሮው ኹሉ የአፍሪካ የነጻነት ፈር ቀዳጅ የጥቁር ሕዝብ ኹሉ ኩራት በሆኑት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ላይ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንደሚያከብር በመተማመን ሕዝባችን በዓሉን በታልቅ ክብር ሲዘክር የዓድዋ ጀግኖችን አንድነት በመውረስ በድርቅ ሳቢያ ለችግር የተጋረጠውን የቦረና ሕዝባችን በአስቸኳይ እንዲታደግ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዚህ ዘመቻ የመጀመሪያውን 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር በመለገስ ፈር ቀዳጅ በመኾኑ የተሰማንን ኩራት እና ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን። በዝርዝር እንመለስበታለን። Via – ያሬድ ሹመቴ #ዓድዋ_127_ለቦረና የማይበላሹ ደረቅ ምግቦችን በመያዝ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ልገሳዎቻችሁን ይዛችሁልን ኑ!!! #ዓድዋ_127_ለቦረና #BORENA #Ethiopia #Guzo_Adwa #ቅድሚያ_ለሰብአዊነት #የሰብአዊ_ድጋፍ_ጥምረት #የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል_ማኅበር “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post