You are currently viewing ሰበር ዜና! አለምገና ሚካኤል የህገወጡ ቡድን መሪ የሆነው አካለወልድ በጣም ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ በሆኑ እና እጅግ በታጠቁ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች  ታጅቦ ሰብሮ ገብቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

ሰበር ዜና! አለምገና ሚካኤል የህገወጡ ቡድን መሪ የሆነው አካለወልድ በጣም ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ በሆኑ እና እጅግ በታጠቁ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች ታጅቦ ሰብሮ ገብቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

ሰበር ዜና! አለምገና ሚካኤል የህገወጡ ቡድን መሪ የሆነው አካለወልድ በጣም ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ በሆኑ እና እጅግ በታጠቁ የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች ታጅቦ ሰብሮ ገብቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ይሄንን ለመቃወም ከሰበታ እና ከተለያየ ቦታ የሚመጡ ወጣቶችን እያፈሱ እና እየበተኑ ይገኛሉ። በአሁን ሰዓት አለምገና ሚካኤል በ ኦሮሚያ ልዩ ሀይል እገዛ በወንበዴዎች ተወሯል ሁሉም ወንበዴዎች ከአለምገና እስከ ሰበታ መንገዱ ተዘግቶ የአለምገና እና የሰበታ ህዝብ እንዳይቃወም በፖሊስ እየታፈሰ እና በመሳሪያ እየተበተነ ነው። ቤተክርስቲያኑ ጊቢ ውስጥ ከ 100 እና 200 የማይበልጡ የእነሱ ደጋፊዎችን አስገብተዋል። ወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ከባድ ተኩስ ተከፍቷል፣ በጥይት ተመተው ጉዳት የደረሰባቸውም እንደሚገኙ ተሰምቷል። በተመሳሳይ ወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ህገወጥ ቡድኖች ተደራጅተው ሰብረው ለመግባት እየሞከሩ እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሱን የምስል መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። ምእመናኑ ባላቸው አቅም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሆን የተቻላቸውን እያረጉ ነው። የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በቀጥታ ቤተክርስቲያኗን ወደ ሚጠብቁ ወጣቶች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፣ ብዙ ወጣቶች በጥይት ተመተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል። አዲስ ሪፖርተር እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply