ሰበር ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በደራ ጅሩ ዳዳ በኩል ከሌሊት ጀምሮ ጦርነት ከፍቷል፤ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግም ተጠይቋል። ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሰ…

ሰበር ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በደራ ጅሩ ዳዳ በኩል ከሌሊት ጀምሮ ጦርነት ከፍቷል፤ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግም ተጠይቋል። ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ በኩል በተደጋጋሚ ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት እያስከፈለ ያለው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በደራ ወረዳ ጅሩዳዳ ቀበሌ በኩል መጠነ ሰፊ የወረራ ጦርነት መክፈቱ ታውቋል። የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ የሆነ ኃይል በማሰማራት ህዳር 2/2015 ከሌሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ ነው በደራ ነዋሪዎች ላይ የወረራ ጦርነት የከፈተው። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከደራ ያነጋገራቸው ምንጮች እንደሚሉት የሽብር ቡድኑ ጀማ ላይ ያለው ፌደራል ፖሊስም ትዕዛዝ አልተሰጠኝም በማለት ድልድይ ብቻ እየጠበቀ ነው ይላሉ። ወረራውን ተከትሎም ራሱን ብሎም ሴቶች፣ ህጻናትንና አቅመ ደካሞች በጨካኙ ስብስብ እንዳይጨፈጨፉ፣ ሴቶች እንዳይደፈሩ እና እገታ እንዳይፈጸም አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ የአልሞት ባይ ተጋድሎ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል የአካባቢው ምንጮች። የአካባቢው ሚሊሻ እና አርሶ አደርም ዘመናዊ እና የቡድን መሳሪያ ከታጠቀ እና ከፍተኛ ኃይል በማሰማራት መጠነ ሰፊ የወረራ ጦርነት የከፈተውን የሽብር ቡድን ለመመከት መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው የሚሉት ምንጮች መከላከያም ሆነ የፌደራል ፖሊስ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል። የአካባቢው ሚሊሾች እና አርሶ አደሮችም የሽብር ቡድኑ በየጊዜው አነጣጥሮ በሚፈጽምባቸው እገታ እና የወረራ ጥቃት ለከፍተኛ ጉዳት እየተዳረጉ መሆናቸው ቢታወቅም የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት የህዝቡን ተደጋጋሚ የድረሱልን፣ መንገድ አስከፍቱልን፣ የታገቱትን አስለቅቁልን እና ኃይል መድቡልን የሚለውን ለቅሶ እና ጭሆት በአግባቡ አዳምጦ ፈጥኖ በቂ ኃይል ለማስፈር ባለመቻሉ ከፍተኛ የሆነ የህይወት እና ቁሳዊ ውድመት እያጋጠማቸው መሆኑም ተወስቷል። በደራ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ተዋቅሮ አማራዊ ማንነቴ እና የወሰን ጥያቄዬ ይመለስ በሚል የሚያደርገውን ህጋዊ መሰረት ያለው ሰላማዊ የሆነውን ትግል ለማዳከም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም የተዋቀረውን ኮሚቴ አመራሮች እና አባላትን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በመግደል፣በማሰር እና በማሳደድ ላይ መጠመዱ ይታወቃል። ምንጭ አሚማ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply