You are currently viewing ሰበር ዜና!  አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሀሮ ሀቦ አካባቢ በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን አሰማርቶ በአማራ ገበሬዎች እና ሚሊሾች ላይ ተኩስ ከፈተ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

ሰበር ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሀሮ ሀቦ አካባቢ በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን አሰማርቶ በአማራ ገበሬዎች እና ሚሊሾች ላይ ተኩስ ከፈተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

ሰበር ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሀሮ ሀቦ አካባቢ በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን አሰማርቶ በአማራ ገበሬዎች እና ሚሊሾች ላይ ተኩስ ከፈተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወለጋን ጨምሮ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ማንነታቸውን እንደ ወንጀል በመቁጠር የአማራ ተወላጆችን በጅምላ እየፈጀ፣ እያፈናቀለ፣ እየዘረፈ እና እያሳደደ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሽህ የሚቆጠር ኃይሉን በማሰማራት በሀሮ ሀቦ አካባቢ ተኩስ መክፈቱ ተሰምቷል። የሽብር ቡድኑ የቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም የተለመደ የወረራ ጥቃቱን የጀመረው ጥቅምት 16/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ራሳቸውን፣ህጻናትንና ሴቶችን ከጭፍጨፋ ለመታደግ ጥረት እያደፈጉ ያሉ ገበሬዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በጃርቴ እና በጃርዴጋ ከተሞች መካከል በሚገኘው በሀሮ ሀቦ ቀበሌ ተኩስ ስለመኖሩ ለማወቅ ተችሏል። በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ካሉት ከ32 ቀበሌዎች መካከል:_ ጃርዴጋ ከተማ፣ ቂልጡ ጬካ እና ደርጌ ኮቲቻ ብቻ ናቸው በሽብር ቡድኑ ቁጥጥር ስር ያልገቡት። ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል አሚማ ያነጋገረው አመራር መስከረም 12/2015 በኦነግ ሸኔ ወረራ ስር የነበረው የጃርቴ ከተማ ተመልሶ በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከሆነ መሰንበቱን አስታውቋል። በጃርዴጋ በግምት በ7 ኪ/ሜትር ርቀት ባለው በሀሮ ሀቦ የተጀመረውን የወረራ ጥቃት ለመቀልበስም ከአካባቢው ሚሊሾች ጋር በመተባበር በተለይም ከርቀት ሽፋን በመስጠት ረገድ እያገዙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን ኋላቀር መሳሪያ የያዘ ገበሬ እና ሚሊሻ ሚስቱ፣ልጆቹ እና ቤተሰቦቹ በጨካኞች እንዳይጨፈጨፉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲታገል ደመወዝ ተከፋይ ልዩ ኃይሎቹ ሚናቸው ሽፋን በመስጠት ላይ መወሰኑ አሳዛኝ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። “ውረዱ እንውረድ” ተባብለው የመጡ ይመስል የኦሮሚያ የልዩ ኃይል አባላት ከጃርቴ ወደ ጃርዴጋ ከማቅናታቸው በተወሰነ የሰዓት ልዩነት ተኩስ መጀመሩ እንደገረማቸው ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። አሚማ አመሻሹን ያጣራው መረጃ እንዳመለከተው በተኩሱ መሀመድ ተሾመ የተባለ አርሶ አደር እግሩ ላይ ሲቆስል በአንጻሩ ወረራ ከፈጸመው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን 3 አባላቱ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸው እና ቡድኑም እየሸሸ ስለመሆኑ ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply