You are currently viewing ሰበር ዜና! እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “አምስቱ የአደራ እስረኞች” ሲፈጸምባቸው ከሰነበተው የግፍ እስር ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …   ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም…

ሰበር ዜና! እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “አምስቱ የአደራ እስረኞች” ሲፈጸምባቸው ከሰነበተው የግፍ እስር ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም…

ሰበር ዜና! እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “አምስቱ የአደራ እስረኞች” ሲፈጸምባቸው ከሰነበተው የግፍ እስር ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ለመተማ የገንዳውሃ እና አካባቢው ነዋሪዎችን፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሆነው ድምጽ የሆኗቸውን ወገኖችን በሙሉ በማመስገን ስለተፈጸመባቸው ዘርፈ ብዙ በደል መረጃ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያጋሩት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ መፈታታቸውን አረጋግጠዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መፈታታቸውን ተከትሎም በስልክ አግኝቶ ስለነበረው አጠቃላይ ሁኔታ አነጋግሯቸዋል። ከባህር ዳር እና አካባቢው ወደ መተማ ገንዳውሃ ተወስደው የሀሰት ክስ ሲቀርብባቸው የሰነበቱት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ በአደራ እስረኝነት መልክ መቆየታቸውን ገልጸዋል። አሚማ ከፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ ከእሸቱ ጌትነትና ከመታገስ ጸጋው ጋር ካደረገው ቆይታ እንደተረዳው ባህር ዳር እና አካባቢው በተያዙበት ወቅት ድብደባን ጨምሮ አያሌ ግፍ እና በደል ተፈጽሞባቸዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ፍ/ቤት እንድትፈቱ ቢወስንም ከበላይ እንዳልፈታ ታዝዣለሁ በማለት በግፍ እስር ያቆያቸው ወጣቶቹ ዛሬ የተፈቱት በትግል መሆኑን ተናግረዋል። ድብደባ እና በጫካ ውስጥ አሰቃቂ ምርመራ የተደረገባቸው መሆኑንም ገልጸዋል። ከግፍ እስር ገንዳውሃ ላይ የተፈቱትም:_ 1) ፋኖ ጥላሁን አበጀ_ የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) አመራር፣ 2) እሸቱ ጌትነት_የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አወማ) ፕሬዝዳንት፣ 3) መታገስ ፀጋው፣ 4) ፋኖ ናትናኤል ዘነበ_የአርበኛ ዘመነ ካሴ አጃቢ እና 5) ኃይለ ማሪያም ክብረት የተባሉ ወጣት ታጋዮች ናቸው። ከግፍ እስር ሲወጡም የገንዳውሃ እና አካባቢው ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ፋኖዎች፣በመንግስት መዋቅር ያሉ ወንድም እና እህቶች ጭምር ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply