ሰበር ዜና !! ======= ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ! ///… አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 13/2013ዓ.ም ባህርዳር //…

ሰበር ዜና !! ======= ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ! ///… አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 13/2013ዓ.ም ባህርዳር /// የሕግ ባለሞያዎች በየአሕጉረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያን ውክልና እየተሰጣቸው ግፈኞችን እንዲፋረዱ ወሰነ፤ • በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመሩ ኹለት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ሰላም መንግሥትንና የፖሊቲካ ኃይሎችን በቀጥታ ያነጋግራሉ፤ • የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን የመዘርጋቱ ሥራ፣ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሠወረት በአስቸኳይ እንዲጀመር ጠቅላይ ጽ/ቤቱን አሳሰበ፤ • ለድንገተኛ አደጋዎች እና ችግሮች ፈጣን ምላሽ እና ርዳታ የሚሰጥ አስተባባሪ አካል፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በማእከል እንዲቋቋም መመሪያ ሰጠ፤ በተለይ የውጭ አሕጉረ ስብከት፣ ኹለገብ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ ያስተባብሩለታል፡፡ Hara Tewahdo-ሐራ ተዋኅዶ

Source: Link to the Post

Leave a Reply