You are currently viewing ሰበር ዜና! ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በተደራጀ መልኩ እየተገደሉ፣እየተዘረፉና እየተፈናቀሉ ያሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች ከአርጆ ጉደቱ እንዳይወጡ ተከለከ…

ሰበር ዜና! ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በተደራጀ መልኩ እየተገደሉ፣እየተዘረፉና እየተፈናቀሉ ያሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች ከአርጆ ጉደቱ እንዳይወጡ ተከለከ…

ሰበር ዜና! ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በተደራጀ መልኩ እየተገደሉ፣እየተዘረፉና እየተፈናቀሉ ያሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች ከአርጆ ጉደቱ እንዳይወጡ ተከለከሉ፤ በርሃብና በኦነግ ሊያስጨርሱን ነው ሲሉ ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በተለይም ከምስራቅ ወለጋ፣ ከሆሮ ጉድሩ፣ ከምዕራብ ወለጋ እና ከምዕራብ ሸዋ ዞን የተለያ ዩ ረዳዎች ዲጋ ወረዳ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በተደራጀ መልኩ እየተፈናቀሉ ያሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። እንደአብነትም ቅሬታ አቅራቢዎች በምስራቅ ወለጋ ዲጋ ወረዳ ከህዳር 2 ቀን 2014 ጀምሮ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል ይጠቅሳሉ። በምስራቅ ወለጋ ዞን አቶ ታከለ የተባሉ የዲጋ ወረዳ አስተዳዳሪም የአሸባሪውን ኦነግ ሸኔ አላማ ተቀብለው በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ የሚሉት ተጎጅዎች ከቀብር አስፈጻሚነት ያለፈ ሚና የላቸውም ሲሉ ይወቅሳሉ። አሁን ደግሞ ነሌሊት ከተደራጀው የመንግስት አካላትና ነዋሪዎች ጭምር ከተሳተፉበት ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ዘረፋ ተርፈን አርጆ ጉደቱ የደረስን ቢሆንም መስተዳድሩ አንድም የሰብአዊ እርዳታ ሊያቀርብ አልቻሉም ብለዋል። መስተዳድሩ እዛው እንዳያስገድለን የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው የገለጹት ከሞት የተረፉ ነዋሪዎች በእነ አቶ ታከለ ትዕዛዝ አዲስ አበባ ዙሪያ፣ሆለታ፣ ነቀምትና ሌሎችም አካባቢዎች የደረሱ ተፈናቃዮች በፖሊስ ተገደው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በትንሹ ከ30 በላይ አማራዎች በግፍ ሲገደሉ እና ከ10 በላይ አድራሻቸው ሲጠፋ እንዲሁም ቀብር ለማስፈጸም ያልቻለ መስተዳድር ሊያስጨርሰን ካልሆነ በስተቀር በምን ሞራሉ ነው “እኔ አለሁ!” ብሎ የመንቀሳቀስ መብታችን ሊገድብ የሚችለው ሲሉም ጠይቀዋል። ከአርጆ ጉደቱ ሲወጡ፣ ነቀምት፣ አዲስ አበባ ዙሪያና ሆለታ ከደረስን በኋላ መታወቂያችሁ ስለተቃጠለ አታልፉም ተብለን በኦሮሚያ ፖሊስ ተገደን ወደ ዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ እንድንመለስ የተደረግነው ከ8 መኪና ሙሉ አማራዎች እንሆናለን ብለዋል። በጥቅሉ አባዎራ ብቻ ከ800 በላይ የሚሆን በሽህ የሚቆጠር አማራ ያለማንም ድጋፍ ሰጭ፣ “በማን መሬት ላይ የሰራህው ቤትና ያፈራህው ንብረት ነው፣ ዝም በል!” በሚል ማስፈራሪያ ጭምር የግፍ ግፍ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጸዋል። አንዲት የ2 ዓመት ህጻን ከተገደለች 3 ቀናትን ካስቆጠረች እናቷ ጡት እየጠባች የመገኘቷ አሳዛኝ መረጃም ለአሚማ ደርሷል። ገዳዮቹ በእናቷ እቅፍ ስር የነበረች ህጻን ልጇን ከትክሻዋ እና አንገቷ ላይ በስለት ወግተው ሞታለች በሚል ጥለዋት እንደሄዱ ተነግሯል። አሁንም በቂ ህክምና እየተደረገላት አይደለም፤ መስተዳድር ላይ ያሉ አካላት ከማውራት ያለፈ እንደ መሪ ሳይሆን ቢያንስ እንደሰው ማድረግ ያለባቸውን ለማድረግ ፍቃደኛ አይደሉም፤ በርሃብና በኦነግ ሊያስጨርሱን ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ስላለብን የሚመለከተው አካል ይርዳን ሲሉ ተማጽነዋል። የሽብር ቡድኑን ይተባበራሉ፤ የንጹሃን አማራዎች እልቂት ምንም አይመስላቸውም ነገር ግን የዲጋ ወረዳ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ናቸው ተብለው በብልጽግና መሾማቸው የተነገረላቸው አቶ ሙላቱ “ስብሰባ ላይ ነኝ” በማለት መረጃ ለመስጠት አልፈቀዱም። የመንግስት ደመወዝ እየበሉ ለአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ስራ አስፈጻሚነት እየሰሩ ነው የተባሉት የዲጋ ረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታከለ የተነሳባቸውን ቅሬታ እንዲያስተባብሉ፣ በግፍ ስለተጨፈጨፉት፣ በጫካ ስለቀሩት፣ ከአርጆ እንዳይወጡ ስለተከለከሉት፣ ከነቀምት፣ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከሆለታ እንዲመለሱ ስላስደረጓቸው በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች እጣ ፈንታና ስለሰብአዊ እርዳታ ማብራሪ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ አልሆኑም። መጀመሪያ መንገድ ላይ ነኝ ካሉ በኋላ አሚማ ደጋግሞ ሲደውልላቸው የሚጠራ ስልካቸውን ሳያነሱ ተመልሰው በመደወል ወደ አርጆ ካልመጣችሁ መረጃ አንሰጥም የሚል አሳፋሪ ምላሽ በመስጠት ስልካቸውን ዘግተዋል። ዝርዝሩን በአሚማ የዩቱብ አዳራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply