You are currently viewing ሰበር ዜና ከወራት በፊት ከ20 በላይ አማራዎች ተገድለው ወደ ወንዝ በተጣሉበት ስቡስሬ ወረዳ የቦቆጅማ ቀበሌን የተቆጣጠረው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በንጹሃን አማራዎች ላይ ግልጽ ጦርነት ከፍቷል።…

ሰበር ዜና ከወራት በፊት ከ20 በላይ አማራዎች ተገድለው ወደ ወንዝ በተጣሉበት ስቡስሬ ወረዳ የቦቆጅማ ቀበሌን የተቆጣጠረው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በንጹሃን አማራዎች ላይ ግልጽ ጦርነት ከፍቷል።…

ሰበር ዜና ከወራት በፊት ከ20 በላይ አማራዎች ተገድለው ወደ ወንዝ በተጣሉበት ስቡስሬ ወረዳ የቦቆጅማ ቀበሌን የተቆጣጠረው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በንጹሃን አማራዎች ላይ ግልጽ ጦርነት ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ ከወራት በፊት ከ20 በላይ አማራዎችን በአሰቃቂ መልኩ በመግደል ወደ ወንዝ ጥለውባታል_በምስራቅ ወለጋ ዞን ስቡስሬ ወረዳ ቦቆጅማ ቀበሌ። በወረዳው ቦቆጅማ ቀበሌ ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ድንገት ከተማዋን በመክበብ ግልጽ ጦርነት ከፍቶ እየጨፈጨፈ ነው ይላሉ ሽህዎች እንደሚሆኑ ለአሚማ በስልክ የገለጹት ተፈናቃዮች ከጫካ። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ልብስ የለበሱ ጭምር እንዳሉበት የሚናገሩት ምንጮች በርካታ ንጹሃን ስለመጨፍጨፋቸውና እነሱም ከጥቃቱ ለማምለጥ በሩጫ ወደጫካ መግባታቸውን ይናገራሉ። ነገሩ እንዲህ ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ:_ “ጥቅምት 1 ቀን 2014 ጀምሮ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ሚሊሾች ከቦቆጅማ ወደ ስቡስሬ ወረዳ ወጡ፤ የኦሮሞ ተወላጆች በሙሉም ተከታትለው ወጡ፤ እኛም ለአማራው የታሰበለት የሞት ድግስ አለ በሚል ለመውጣት ስንሞክር በአራት አቅጣጫ በር ተዘጋብን” ይላሉ። አንዳንድ የኦነግ ሸኔ አባላትም እቃ ለመውሰድ ወደ ቦቆጅማ ሲመለሱ “እናንተ ትኖራላችሁ አይደለ?” እያሉ ይዝቱባቸው እንደነበር ገልጸዋል። በመጋቢት ወር 2 ባለሞተሮች፣ በሀምሌ ደግሞ ሼህ ሰይድ የተባሉ አባት፣ በነሃሴ ወር ደግሞ 16 ከበቆሎ ማሳቸው እንዳሉ፣ ሌላም አንድን ሰው ጨምረው በድምሩ 20 አማራዎችን አፍነው በግፍ በመግደል ወደ ወንዝ መጣላቸው ተወስቷል። በቦቆጅማ በአሁኑ ሰዓት የሞተው ሞቶ፣ የሸሸውም ሸሽቶ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እየተለበለበች ትገኛለች ብለዋል፤ ብዙ አማራዎችን ጨፍጭፈዋል ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በተለይ በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በርካታ ጸረ አማራና ጸረ ሀገር የመንግስት አካላት ከሽብር ቡድኑ ጋር በመሆን በአማራዎች ላይ የጀመሩትን እልቂት አጠናክረው በማስቀጠል ላይ ናቸው፤ ይህም በ16ኛው ክ/ዘመን ሲያደርጉት የነበረው በጅምላ እየገደሉና እያረዱ የመስፋትና የመንሰራፋት፣ የመዝረፍ ዘላቂ ውጤት የማያመጣ የባለከንቱ እሳቤ ተሸካሚዎች መንገድ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply