
ሰበር ዜና! ከጃርዴጋ ለቀው በገጠራማ ቀበሌዎች በሚገኙ አማራዎች ላይ ተስፋፊ፣ አሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን ዳግማዊ ጥቃት እየፈጸሙ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጃርዴጋ ከተማ እየኖሩ ሳለ በተፈጸመባቸው ጥቃት ለቀው ወደ ገጠር ቀበሌዎች የሄዱ አማራዎች ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ጥቃቱም የተከፈተው በአሸባሪ፣ ወራሪ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን የካቲት 6/2015 ሲሆን በለገሜጫ፣ጫቶ፣ ሽሉኬ እና በሀሮ ሀቦ በተባሉ አራት አካባቢዎች ነው። ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየቀጠለ ያለው ጥቃት ከፍተኛ የህይወት እና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ በፊት የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው እየተሳደዱ ያሉ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
Source: Link to the Post