You are currently viewing ሰበር ዜና! “ከፋኖ ጎን ለመሰለፍ ከሆነ እንጅ ከፋኖ ጋር እርስ በርስ ለመዋጋት የምንወስደው ስልጠና አይኖርም” በሚል ስልጠናውን አፍርሰው ከአዳርቃይ እየተመለሱ የነበሩ ፖሊሶች እና የሚሊሻ…

ሰበር ዜና! “ከፋኖ ጎን ለመሰለፍ ከሆነ እንጅ ከፋኖ ጋር እርስ በርስ ለመዋጋት የምንወስደው ስልጠና አይኖርም” በሚል ስልጠናውን አፍርሰው ከአዳርቃይ እየተመለሱ የነበሩ ፖሊሶች እና የሚሊሻ…

ሰበር ዜና! “ከፋኖ ጎን ለመሰለፍ ከሆነ እንጅ ከፋኖ ጋር እርስ በርስ ለመዋጋት የምንወስደው ስልጠና አይኖርም” በሚል ስልጠናውን አፍርሰው ከአዳርቃይ እየተመለሱ የነበሩ ፖሊሶች እና የሚሊሻ አባላት ወገራ በሰፈረው የአገዛዙ ጦር ተኩስ ተከፈተባቸው፤ አንድ የፖሊስ አባል መቁሰሉ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ከፋኖ ጎን ለመሰለፍ ከሆነ እንጅ ከፋኖ ጋር እርስ በርስ ለመዋጋት የምንወስደው ስልጠና አይኖርም” በሚል በአዳርቃይ የነበረውን የስልጠና መርሃ ግብርን በርካቶች አፍርሰው መውጣታቸው ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ምንጮች እንደገለጹት አገዛዙ አንድ ብርጌድ በማወቀር እና በማሰልጠን በፋኖ ላይ ለመዝመት ብሎም እርስ በርስ ለማዳማት አቅዶ እየሰራ ነበር፤ አዳርቃይም ለስልጠና በሚል ከተጠሩት መካከል እስከ 2 ሽህ የሚሆኑት በስፍራው ተገኝተው ነበር። ከመግባታቸውም የስልጠናው አላማ ሲነገራቸውም:_ የአገዛዙን እድሜ ለማስቀጠል ሲባል የህልውና አደጋ የገጠመውን የአማራ ህዝብ የበለጠ የሚያጎሳቁል፣ ከፋኖ ጋር እርስ በርስ የሚያዋጋ እና ለጠላት ምቹ መደላድል የሚፈጥር ታሪካዊ ስህተት የሚያሰራ አካሄድን አንቀበልም በማለት ሀምሌ 10/2015 ስልጠናውን አፍርሰው መመለሳቸው ተገልጧል። ከመካከላቸውም ከ40 በላይ የሚሆኑት ከአዳርቃይ በጎንደር በኩል ሲመለሱ ወገራ ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ አካባቢ የሰፈሩ የብልጽግና አገዛዝ ተልዕኮ ፈጻሚ በሆኑ የመከላከያ አባላት ተኩስ ተከፍቶባቸዋል፤ በጥቃቱም አንድ የፖሊስ አባል መቁሰሉ ታውቋል። ከአዳርቃይ ፈርሰው የወጡ እነዚህ ፖሊሶች እና ምልምል ሚሊሾች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ ከአምባ ጊዮርጊስ ከተማ በግምት ከ3 እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ጅብ ዋሻ በተባለ አካባቢ የሰፈሩ የአገዛዙ አካላት ናቸው ኬላ ዘግተው አናሳልፍም በማለት ነው ተኩስ ከፍተው ጉዳት ያደረሱት ተብሏል። የቆሰለው የፖሊስ አባልም የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ተሰምቷል። ሌሎቹ ፖሊሶች እና የሚሊሻ አባላት በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አሚማ እያጣራ መረጃ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply