ሰበር ዜና! ወደ ደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ያቀኑት የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ታሰሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝ…

ሰበር ዜና! ወደ ደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ያቀኑት የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ታሰሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ሚያዝያ 12/2014 ወደ ደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ለሀገር አቀፍ ፓርቲነት የድጋፍ ፊርማ ለማሰባሰብ ያቀኑ መሆናቸው ይታወቃል። ይሁን እንጅ ህዝብ ሰብስበው መምከር እንደማይችሉ ክልከላ ቢደረግባቸውም በአርባ ምንጭ ከተማ እየተዟዟሩ ከነዋሪው በተለይም ከወጣቶች የሀገር አቀፍ ፓርቲነት የድጋፍ ፊርማ ሲያሰባስቡ መዋላቸው ተገልጧል። ነገር ግን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ጋር ያደረገው ቆይታ እንዳመለከተው አመሻሹን የአርባ ምንጭ ከተማ የሰላም እና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ፍቃድ የላችሁም ከማለት ባሻገር “አካሄዳችሁ አልተመቸንም” በማለት የባልደራስ ፕሬዝደንት እነ አቶ እስክንድር ነጋንና ሌሎች አመራር እና አባላት በአርባ ምንጭ ፖሊስ ጣቢያ ማሰራቸው ታውቋል። ከአቶ እስክንድር ነጋ በተጨማሪ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው እና ሱራፌኤል አንዳርጌ መታሰራቸው ተገልጧል። አሚማ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘ ተከታትሎ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply