ሰበር ዜና! የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን በመተከል ዞን ከዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ አካባቢ በጉምዝ ታጣቂዎች የታገቱትን የጤና ባለሙያዎችን ማስለቀቁ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

ሰበር ዜና! የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን በመተከል ዞን ከዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ አካባቢ በጉምዝ ታጣቂዎች የታገቱትን የጤና ባለሙያዎችን ማስለቀቁ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

ሰበር ዜና! የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን በመተከል ዞን ከዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ አካባቢ በጉምዝ ታጣቂዎች የታገቱትን የጤና ባለሙያዎችን ማስለቀቁ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ከዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ቁጥር 3 በተባለች የገጠር ቀበሌ አካባቢ ባለጫካ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት በመኪና ሲጓዙ በነበሩ የጤና ባለሙያዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የጉምዝ ታጣቂዎች ባለሙያዎችን አግተው መውሰዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። 50 ኪሎ ሜትር ርቀት በእግራቸው አቆራርጠው ወደ በላያ ቀበሌ ማቅናታቸው የተገለፀ ሲሆን በነገው እለት ከቤረሰብ ጋር እንደሚቀላቀሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መከላከያ ሰራዊት አፋኙን ለይቶ በመምታት ኦፕሬሽን ነው ያተረፋቸው የተባለ ሲሆን ከመካከላቸው ወንዱ የቆሰለ ስለመሆኑ መስማቱን ነው የመረጃ ምንጫችን የገለፀው። በሌላ በኩል የአንድ ሰው ህይወት አልፏል የሚል ዘገባም በማህበራዊ ሚዲያ ተዘግቧል። የታጋቾች ስልክ እንደሰራልን ስለቆይታቸውና ስለደረሰው ጉዳት የምናነጋግራቸው ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply