ሰበር ዜና! የምስራቅ አማራ ፋኖ ሊቀመንበር ፋኖ ምህረት ወዳጆ እና አብረዋቸው ከደሴ ወደ ወልዲያ የተጓዙ ፋኖዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ በንግግር የተፈታ መሆኑ ተገለጸ። አማራ…

ሰበር ዜና! የምስራቅ አማራ ፋኖ ሊቀመንበር ፋኖ ምህረት ወዳጆ እና አብረዋቸው ከደሴ ወደ ወልዲያ የተጓዙ ፋኖዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ በንግግር የተፈታ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አማራ ፋኖ ሊቀመንበር ፋኖ ምህረት (ምሬ) ወዳጆ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ እንደገለጹት ሚያዚያ 2/2014 ከሰዓት በኋላ ከትግል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ከደሴ ወደ ወልዲያ ተጉዘዋል። ይሁን እንጅ ወልዲያ እንደደረሱ በመግቢያ አካባቢ ጠብቀው የቆዩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እነ ፋኖ ምሬ ወልዲያ የታሰሩ የፋኖ አባላትን በኃይል ለማስፈታት እየመጡ ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ ትጥቅ ለማስፈታት ሞክረዋል ተብሏል። ፋኖ ምሬ ወዳጆ የሚመሩት የምስራቅ አማራ ፋኖ ግን ትጥቁን ለመፍታት ፍቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ ከመከላከያ አመራሮች ጋር ወልዲያ ስታዲዬም አካባቢ ለ1 ሰዓት የዘለቀ ውይይት ከተደረገ በኋላ በመግባባት ተለያይተዋል። በመሆኑም እነ ፋኖ ምሬ አሁን ላይ ትጥቃቸውን አልፈቱም፤ ወደ ወልዲያ ከተማ በሰላም መግባታቸውንም ለአሚማ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በወልዲያ የታሰሩ፣ ድብደባ የተፈጸመባቸውና የተማረኩ የምስራቅ አማራ ፋኖ የየጁ ቅርንጫፍ አባላትን ጉዳይ በተመለከተም የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 4/2014 በወልዲያ ካሉ ከመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር እንደሚወያዩበት ፋኖ ምሬ ለአሚማ አስታውቀዋል። ስለሆነም ለሁሉም በሰከነ መንገድ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን መፍታት እንደሚገባና እንደሚጠቅም የተናገሩት ፋኖ ምሬ መላው የምስራቅ አማራ ፋኖ አባላት፣ የትግሉ ደጋፊዎች፣ የመንግስት አካላትና ህዝቡ ተጨማሪ ዋጋ እንዳይከፈል ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲያዩት ጥሪ አድርገዋል። ሚያዚያ 2/2014 የምስራቅ አማራ ፋኖ የየጁ ቅርንጫፍ ከወልዲያ ህዝብ ጋር ያደርገዋል የተባለው ምክክር በወረዳና በዞን የመስተዳድር አካላትና በመከላከያ ሰራዊት ክልከላ እንደገጠመው ይታወቃል ትዕዛዝ የተሰጣቸው የመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶዎችም ሚያዚያ 1/2014 የነበረውን ቅስቀሳ ከመከልከል አልፈው ከ5 በላይ የምስራቅ አማራ ፋኖዎችን አስረዋል፤ አንድ ሰናይፐር እና 5 ክላሽ ወስደውባቸዋል፣ ፋኖ ይርጋ በተባለ አባላቸውና ሾፌራቸው ላይ ከፍተኛ ድብደባ የፈጸሙ መሆናቸውም አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply