
ሰበር ዜና! የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ ተደበደበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 18/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ መደብደቡን የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰውኛል። የአስተዳዳሪውን ቤት በቦንብ የደበደቡት ያልታወቁ ኃይሎች መሆናቸው ታውቋል። በቦንብ ድብደባውም በሰው ላይ ጉዳት አልመድረሱን ለማወቅ ችያለሁ። አሁን ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤትን የዐቢይ አህመድ ወታደሮች እየጠበቁት እንደሆነ የአይን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል። ዘገባው_የጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር ነው።
Source: Link to the Post