ሰበር ዜና! የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ሉአላዊነት መጋፋቱን ቀጥሎ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በጀበል ስኳር ተራራና በአካ…

ሰበር ዜና! የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ሉአላዊነት መጋፋቱን ቀጥሎ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በጀበል ስኳር ተራራና በአካ…

ሰበር ዜና! የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ሉአላዊነት መጋፋቱን ቀጥሎ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በጀበል ስኳር ተራራና በአካባቢው ገበሬዎች ላይ ሲተኩስ ማምሸቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ላለፉት ሳምንታት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ በተለያዩ አካባቢዎች በመግባት ምሸግ ሲቆፍር፣ ባለሀብቱንና አርሶ አደሩን ሲዘርፍ የሰነበተው የሱዳን ጦር ዛሬም በመተማ ቱመት መንዶካ በኩል ሲተኩስ ማምሸቱ ተሰምቷል። ከምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በመተማ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በጀበል ስኳር ተራራ እና አካባቢው በዲሽቃ በመታገዝ ሲተኩሱ አምሽተዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ የአካባቢው ባለሀብቶች እንደገለፁት ቀደም ሲል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ የነበረውን ጀበል ስኳር ተራራን ተቆጣጥረዋል። ከተራራው ስር ያሉ የበርካታ ባለሀብቶች ምርት አለመነሳቱን ያስታወቁት ባለሀብቶቹ ተራራውን ስለያዙባቸው አይደለም ምርቱን ለመሰብሰብ ለህይወታቸውም እንደሚሰጉ ገልፀዋል። እንደአብነት ከተራራው ስር አንድ ባለሀብት ብቻ አመቱን ሁሉ የደከመበትን ከ600 ኩ/ል በላይ ማሽላ አለማንሳታቸው ታውቋል። ቲሃን ተሻግሮ ከኢትዮጵያ መሬት ጀበል ስኳር ተራራ አጠገብ የአቶ በእውቀት ወርቁ ፣የአቤ ታከለ፣የመለስ አለሜ እና ሌሎች ባለሀብቶች ሰፊ አዝመራ እንደሚገኝ ተነግሯል። ለአማራ ሚዲያ ማዕከል መረጃ ያደረሱትም ከመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ አካባቢ ከተከፈተው የሱዳኖች ተኩስ የሸሹ ባለሀብቶች አቶ ሙሉጌታ መኮንን፣ አቶ ደመወዝ ሰጠኝና አቶ በእውቀት ወርቁ ናቸው። መንግስት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥበት የጠየቁት ባለሀብቶቹ የሱዳን ጦር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ነው የገለፁት። ሱዳን ዳር ድንበርን በመጋፋት እያደረገችው ካለው የመስፋፋት እንቅስቃሴ በተጨማሪ በቀን ሰራተኝነት እያገለገሉ ባሉ ኢትዮጵያዊ ሰራተኞች ላይ ዘርፈ ብዙ ተፅዕኖዎችን እየፈጠረች መሆኗን ከቅሬታ አቅራቢዎች ለመረዳት ተችሏል። ሱዳን እያደረገችው ካለው የደመ ነፍስ እንቅስቃሴ በስተጀርባ ማን አለ የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም፤ ብዙዎች ከውጭ የግብፅ እጅ እንደሚኖርበት ሲጠቁሙ፣ ከውስጥ ደግሞ በባንዳነትና በአገር ሻጭነት ሲያገለግል የቆዬውና አሁን ላይ በተወሰደበት ህጋዊ እርምጃ ሸሽቶ ሱዳን የገባው የትሕነግ ዘር አጥፊ ቡድን አለበት ሲሉ ማሳያዎችን ያነሳሉ። በመሆኑም መንግስት በዲፕሎማሲው ረገድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ ሳይዘናጋ ሉአላዊነትን ለማስከበር የሚያስችል የመከላከያ ኃይል በድንበር አካባቢ ማስፈሩ የግድ የሚለው ጊዜ ላይ ስለመሆኑ እየተገለፀ ነው። የአካባቢውን የመስተዳድር አካላትና ባለሀብቶችን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply