You are currently viewing ሰበር ዜና! የቆላድባ ሻለቃ ፋኖዎች በአገዛዙ አካላት በሌሊቱ ተኩስ የተከፈተባቸው መሆኑን አስታወቁ፤ ፋኖ ቻላቸው ንጉሴ እና በላይነህ ሲምር በቆላድባ 02 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤታቸው ተኩስ የተከ…

ሰበር ዜና! የቆላድባ ሻለቃ ፋኖዎች በአገዛዙ አካላት በሌሊቱ ተኩስ የተከፈተባቸው መሆኑን አስታወቁ፤ ፋኖ ቻላቸው ንጉሴ እና በላይነህ ሲምር በቆላድባ 02 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤታቸው ተኩስ የተከ…

ሰበር ዜና! የቆላድባ ሻለቃ ፋኖዎች በአገዛዙ አካላት በሌሊቱ ተኩስ የተከፈተባቸው መሆኑን አስታወቁ፤ ፋኖ ቻላቸው ንጉሴ እና በላይነህ ሲምር በቆላድባ 02 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤታቸው ተኩስ የተከፈተባቸው መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 8/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ የአገዛዙ የጸጥታ አካላት በቆላድባ ፋኖዎች ላይ ሀምሌ 8/2015 ከሌሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ የታቀደ ከበባ በማድረግ ተኩስ የከፈቱ መሆኑ ተገልጧል። ለአሚማ መረጃ የሰጡ ምንጮች እንደሚሉት አፈናው እና የከበባ ተኩስ ከሁሉም በፊት የተከፈተበት በፋኖ ቻላቸው ንጉሴ እና በላይነህ ሲምር መኖሪያ ቤት ላይ ነው። አፋኙ ኃይል ብሬን እና ክላሽ እየተጠቀመ ስለመሆኑ የጠቆሙት ምንጮች በአካባቢው ካሉ ፖሊሶች እና ሚሊሾች በተጨማሪ ሌላ ኃይል አስገብቶ ሊሆን እንደሚችል ጠንካራ ግምት አላቸው። ለአንድ ሰዓት ገደማ ከቆዬው የተኩስ ልውውጥ በኋላም ሌሎች የቆላድባ ሻለቃ አባላት ለሁለቱም ፋኖዎች ሽፋን በመስጠት ከከበባ ለማስወጣት መቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል። የቆላድባ ሻለቃ ፋኖ አመራር እና አባላት ሰኔ 25/2015 ከከተማው ወጣ ብለው ሊያደርጉት የነበረው የምክክር መድረክ በውስን የወረዳ እና የቆላድባ ከተማ ካድሪዎች የተሳሳተ አካሄድ ለጊዜው መደናቀፉንና ነገር ግን ምክክሩ የሚቀጥል መሆኑን ፋኖዎች ለአሚማ መግለጻቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply