You are currently viewing ሰበር ዜና! የብልጽግና ሰዎች የስምምነቱን ቃል ከመተግበር ይልቅ በፋኖ ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተገለጸ፤ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ዳግም ማክሰኝትን፣ የወረዳውን መስተዳድር እና ሚሊሻ ጽ/ቤት…

ሰበር ዜና! የብልጽግና ሰዎች የስምምነቱን ቃል ከመተግበር ይልቅ በፋኖ ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተገለጸ፤ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ዳግም ማክሰኝትን፣ የወረዳውን መስተዳድር እና ሚሊሻ ጽ/ቤት…

ሰበር ዜና! የብልጽግና ሰዎች የስምምነቱን ቃል ከመተግበር ይልቅ በፋኖ ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተገለጸ፤ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ዳግም ማክሰኝትን፣ የወረዳውን መስተዳድር እና ሚሊሻ ጽ/ቤትን ተቆጣጥሯል፤ መንገድም ከእያቅጣጫው በህዝባዊ ኃይሉ እና በወጣቶች ተዘግቷል ተብሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 12/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ያሉ የብልጽግና ሰዎች የስምምነቱን ቃል ከመተግበር ይልቅ በፋኖ ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተገልጧል። ተኩሱ የተጀመረው ሀምሌ 12/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን መነሻውም “ብልጽግና የተደረሰበውን ስምምነት እንደለመደው በመጣስ በወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት በኩል ከፋኖ አደባባይ አበበ የተወሰደውን ትጥቅ/ነፍጥ አልመልስም” በማለቱ ነው ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል። ነገሩ ፋኖን ከሚሊሾች እና ከፖሊሶች ጋር ለማጋጨት የታሰበ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል። በርካታ የወረዳው ሚሊሾችና ፖሊሶችም ከፋኖ ጋር አንዋጋም በማለት እጃቸው ከደሙ ንጹህ መሆኑን ለማሳዬት እየሸሹ መሆናቸው ተሰምቷል። ፋኖ ዳግም የወረዳውን መስተዳድር እና ሚሊሻ ጽ/ቤትን ተቆጣጥሯል፤ መንገድም ከእያቅጣጫው በህዝባዊ ኃይሉ እና በወጣቶች ተዘግቷል ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ ማክሰኝት እንደገና “በአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ” ቁጥጥር ስር ውሏል። ፋኖዎችም ማህበረሰቡ ከእነሱ ጎን እንዲሆን ጥሪ አድርገዋል። አሚማ ተጨማሪ መረጃ የሚያናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply