ሰበር ዜና! የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥቅምት 18 እና 22 ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለጋዜጠኞች ለመስጠት በሚል ያዘጋጀው ፕሬስ ኮንፈረንስ በፖሊስ ተከለከለ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

ሰበር ዜና! የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥቅምት 18 እና 22 ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለጋዜጠኞች ለመስጠት በሚል ያዘጋጀው ፕሬስ ኮንፈረንስ በፖሊስ ተከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

ሰበር ዜና! የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥቅምት 18 እና 22 ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለጋዜጠኞች ለመስጠት በሚል ያዘጋጀው ፕሬስ ኮንፈረንስ በፖሊስ ተከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥቅምት 18 እና 22 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለጋዜጠኞች ለመስጠት በሚል ያዘጋጀው የፕሬንስ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከልክሏል። ፕሬስ ኮንፈረንሱ በአዲስ አበባ ቤለር አካባቢ በሚገኘው በአብን ዋና ጽ/ቤት ለማካሄድ ለዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ ቢሆን ከሰዓት ጀምሮ የጽ/ቤቱን በር ጨምሮ አካባቢው በአዲስ አበባ ፖሊስ መከበቡን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ቦታው ድረስ ተገኝቶ ሁኔታውን ለመታዘብ የቻለ ሲሆን ጋዜጠኞችንና የአብን አመራሮችን ከቢሮው ግቢ በር እና በአካባቢው አትቁሙ በማለት ሲበትኗቸው ለማስተዋል ተችሏል። የአብን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን አቶ ጣሂር መሀመድን ስላጋጠመው ችግር ማብራሪያ እንዲሰጡን በሚል ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት የሚጠራ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም። አብን በአማራ ክልል ለነገ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በክልሉ መንግስት አልተፈቀደም ቢባልም የማሳወቅ እንጅ የመከልከልና የፈቃጅነት ስልጣን የለውም በሚል በአማራ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዘውን የተቃውሞ ሰልፍ በእቅዱ መሰረት ለማስኬድ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ስለሰልፉ ዝርዝር ሁኔታዎች በዋና ጽ/ቤቱ እየመከሩ ባሉበት ወሳኝ ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበባ በመፈፀም መግባትና መውጣትም አትችሉም የሚል አፈና በመግባቱ የታቀደውን ሰልፍ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት እና ለሰልፉ የተዘጋጁ ሎጂስቲኮችን ለማንቀሳቀስም ሆነ ሰልፉን ለመምራት ስራ አስፈፃሚው ወደ ክፍለ ሀገር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግረናል ሲል አብን ከክልከላ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በዚህ የተነሳም አብን የጠራውን ሰልፍ በኃላፊነት መምራት የማይችል መሆኑን የድርጅታችን አባላት፣ ደጋፊዎችና መላው ሕዝባችን እንድታውቁት እንፈልጋለን። መንግስት አማራ ማዘን እንኳን አይችልም በሚል እርቃን የወጣ አምባገነንነት ውስጥ በመግባቱ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው የትግል አካሄዶችን በተመለከተ የምናሳውቅ መሆኑንም ጨምረን እናሳውቃለን።” ብሏል አብን ባወጣው መግለጫ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply