ሰበር ዜና – የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ማምሻውን መግለጫ አወጣ። ”የፖለቲካ ግልሙትና የሚፈጽሙ እና የሴራ ፖለቲካ እየሸመኑ፣ዘረኝነት እያቦኩ” ያላቸውን መታገል የሚያስፈልግበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል ይላል መግለጫው።ሙሉ መግለጫውን ይዘናል።

ባሕርዳር ከተማበትላንት የታሪክ ምርኮኞችና በነገው ተስፋችን ቁማርተኞች ሕልውናዋን የማታጣ ሃገር መገንባት ከሁላችንም የሚጠበቅ ኀላፊነት ነው።ባሕር ዳር: የካቲት 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምድራችን ካላፉት የሥርዓተ መንግሥታት ታሪክ ውስጥ በራሳቸው ሕዝብ መካከል ተቃርኖን እየሸመኑ አንዱን የማኅበረሰብ ክፍል ከሳሽ፣ ሌላኛውን  ደግሞ ተከሳሽ የሚያደርግ ጥልፍ በመጎንጎን የሀገረ መንግሥትነት ሕልውናቸውን ያጸኑም ሆነ ዘላቂ ሰላምና እድገታቸውን ያረጋገጡ መንግሥታት ተብለው ለአብነት ያህል እንኳ  ስማቸው የሚጠቀስ ነገሥታትም ሆኑ መንግሥታት የሉም። እንዳለመታደል ሆኖ ከታሪክም ሆነ ከአሁናዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የአንድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply