You are currently viewing #ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ አባላት  ማክሰኝት ከተማንና ጎንደር ዙሪያ ወረዳን ተቆጣጣረ‼ ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በፋኖ አለሙ ጎዳዳው የሚመራው የአማራ ፋኖ…

#ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ አባላት ማክሰኝት ከተማንና ጎንደር ዙሪያ ወረዳን ተቆጣጣረ‼ ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በፋኖ አለሙ ጎዳዳው የሚመራው የአማራ ፋኖ…

#ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ አባላት ማክሰኝት ከተማንና ጎንደር ዙሪያ ወረዳን ተቆጣጣረ‼ ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በፋኖ አለሙ ጎዳዳው የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ከከተማው እና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመቀናጀት ባደረገው እንቅስቃሴ የማክሰኝት ከተማን እና የወረዳው ብልጽግናን ጽ/ቤት ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ አባላት ከጎንደር ከተማ በግምት 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ዋና ከተማን ማክሰኝትን እና በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የወረዳው የብልጽግና ጽ/ቤትን ጨምሮ ሌሎች መንግስታዊ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል። የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ አደባባይ አበበ ሀምሌ 10/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ለስራ ጉዳይ በሚል ከማክሰኝት በግምት 1 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በተለምዶ አርባያ መገንጠያ በሚባል አካባቢ በተገኘበት በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኘው የአገዛዙ ጦር መያዙ ይታወቃል። በፋኖ አደባባይ አለሙ አፈና ምክንያት ማክሰኝት እና አካባቢው ከሀምሌ 10/2015 አመሻሽ ጀምሮ ከፍተኛ ውጥረት ነገሶ ነበር። ይህን ተከትሎም የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ አባላት ሀምሌ 11/2015 ከጠዋቱ 1:10 ጀምሮ ነው ማክሰኝት ከተማን መቆጣጠሩ የተገለጸው። ፋኖ ከከተማዋ እና አካባቢው ወጣቶች ጋር በመተባበር መንገድ በመዝጋት እርምጃዎችን ወስዶ ነው ከተማዋን መቆጣጠሩን ለማወቅ የቻልነው። ከተማዋን ለመያዝም ከሀምሌ 11/2015 ከጠዋቱ 12:30 ገደማ በመጀመር ባደረገው የተናበበ እንቅስቃሴ ከ30 ደቂቃ ያልበለጠ ጊዜ ስለመውሰዱ ነው የተገለጸው። ስጋቱ ያላቸው የወረዳው አመራሮችም ከማክሰኝት ከተማ ሸሽተው ወደ ሌላ አካባቢ ስለመውጣታቸው ተሰምቷል። ይሁን እንጅ በአገዛዙ ጦር አፈና ስር የሚገኘውን ፋኖ አደባባይን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ለማስለቀቅ አለመቻሉ ተገልጧል። ከጎንደር ወደ ማክሰኝት እና ከማክሰኝት ወደ ባ/ዳር የሚወስደው መንገድ ለጊዜው የተዘጋ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ፋኖ በወረዳው ተቋማት ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር እየጠበቀ ስለመሆኑ አስታውቋል። የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደውም በአገዛዙ ጦር የታፈነበትን አመራር አደባባይ አበበን ለማስለቀቅ ይሁን እንጅ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የድርሻውን ለማበርከት በማለም የተደራጀ እና በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ህዝባዊ አደረጃጀት መሆኑ ታውቋል። ይህን ተከትሎም አገዛዙ በጎንደር አዘዞ የሚገኝ ኃይሉን በማንቀሳቀስ ወደ ማክሰኝት በማስጠጋት ላይ ስለመሆኑ መረጃ እንዳለው ፋኖ አስታውቋል። በተጨማሪም ከባህር ዳር ከዋና ሰሜን ምዕራብ ማዘዣው በርካታ ኃይሉን እያንቀሳቀሰ ነው፤ በተያያዘም የጎንደር ዙሪያ ወረዳ አመራርም ከፋኖ ጋር አንዋጋም ያሉትን ወደ ጎን በመተው ታዛዥ የጸጥታ አካላትን ማለትም ሚሊሺያና ፀረ ሽምቅ መልምሎ በማሰባሰብ በአርባያ መገንጠያ በኩል እየተጠጋ መሆኑ ተገልጧል። የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ያገባኛል የሚል ሁሉ ከትግሉ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ቀርቧል። መረጃው የአሚማ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply