ሰበር ዜና! የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…     ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ የአገር መከላከ…

ሰበር ዜና! የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአገር መከላከ…

ሰበር ዜና! የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአገር መከላከያ ሰራዊት በከሃዲው ሕወሓት ላይ መቀሌን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን 3ኛውንና የመጨረሻውን ምዕራፍ ህግ የማስከበር እርምጃ በመውሰድ ከ7 ሺህ በላይ የሰሜን እዝ አባላትን ነጻ አውጥቷል ያሉት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ናቸው። የሰሜን እዝ ማዘዣ ጣቢያን የተቆጣጠረው የመከላከያ ሰራዊት በየስርቻው የተደበቁትን ተፈላጊ የህወሃት ጁንታ አባላትን እያደነ ይገኛልም ተብሏል። ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ማምሻውን መግለጫ የሰጡት ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ከሰዓት በኋላ መቀሌን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል መላው የትግራይ ህዝብ እንኳን ነጻ ወጣችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት ተችሏል”ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ የመከላከያ ሠራዊት በድል በገሠገሠባቸው የትግራይ አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር ማሳየቱን ገልፀዋል። ሕወሓት ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቀሌ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ እንዳደረገና ይህም የሠራዊቱን ድል ሲያፋጥን ለከሃዲው ቡድን ግን ሽንፈቱ አፋጥኖታል ነው የተባለው። ቡድኑ በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን እያወደመ መሄዱንም የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ እንደማይመጥነው አስታውቀዋል። ቡድኑ እኔ ከሞትኩ ብሎ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply