ሰበር ዜና! የእነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አመራሮችን ችሎት ለመታደም ወደ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ያቀኑ 5 የባልደራስ አባላትና የተከሳሽ ቤ…

ሰበር ዜና! የእነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አመራሮችን ችሎት ለመታደም ወደ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ያቀኑ 5 የባልደራስ አባላትና የተከሳሽ ቤተሰቦች ታሰሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከእነ እስክንድር ነጋ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ጋር ያደረገው ቆይታ እንዳመለከተው ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በእስር ላይ እያሉ የእነ እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌን ችሎት ለመታደም ያቀኑ 5 የድርጅቱ አባላትና የተከሳሽ ቤተሰቦች በልደታ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል። የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ቤተሰቦች የታሰሩት የነገስታት ምስል እና አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያለበት ልብስ በመልበሳቸው የተነሳ ነው ያሉት ጠበቃ ሄኖክ ይህ ያልተገባ ወከባ እና እስር ነው ሲሉ አውግዘውታል። በዚህም ናትናኤል ያለምዘውድን ጨምሮ 5 የባልደራስ አባላትና የተከሳሽ ቤተሰቦች በልደታ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ስለመታሰራቸው የገለፁት ጠበቃ ሄኖክ ወደ ጣቢያው አቅንተው እንደሚጠይቁም አስታውቀዋል። ችሎት ለመታደም በመጡ የባልደራስ አባላትና የተካሳሽ ቤተሰቦች ላይ የሚደርሰው ወከባ እና እስር እነ አቶ እስክንድር ነጋንና ስንታየሁ ቸኮልን በማስቆጣቱ ለፍ/ቤቱ አቤቱታ እንዲያቀርቡ አድርጓቸዋል ብለዋል። አቶ እስክንድር ነጋ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዴራ ማድረግ ወንጀል ነው ወይ? ይህ አካሄድ መታረም አለበት ሲሉ ያሳሰቡ ሲሆን አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ መያዝ ወንጀል የሆነበት በትናንቱ የህወሀት ስርዓት ነው፤አሁንም የህወሃት ስርዓት ከተወገደ በኋላም በስልጣን ላይ ያሉ አካላት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዴራና የኢትዮጵያ ነገስታትን ምስል እያዩ መከልከላቸው ከህወሃት አለመለየት ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ በተነሳው ቅሬታ ላይ ምላሽ ለመስጠት በሚል ለቀጣይ አርብ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ስለመስጠቱ ነው የተነገረው። ጠበቃ ሄኖክ ይሄ ችሎትን ለመከታተል የሚመጡ የተከሳሽ ቤተሰቦችን ማጉላላትና ማዋከቡ እየተደጋገመ መሆኑ ጠቅሰው አካሄዱ ትክክል አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply