ሰበር ዜና! የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በሆሮ ጉድሮ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ኢዶኪሳ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…  ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ….

ሰበር ዜና! የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በሆሮ ጉድሮ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ኢዶኪሳ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ….

ሰበር ዜና! የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በሆሮ ጉድሮ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ኢዶኪሳ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በሆሮ ጉድሮ ዞን አቢደንጎሮ ወረዳ ኢዶኪሳ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑት በአቶ ኡመር ይብሬ በተባሉ የቀበሌ ሚሊሻ ኮማንደር ቤትን በመክበብ ተኩስ ከፍተዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቅድሚያ በአቶ ኡመር ይብሬ ቤት ላይ በተደጋጋሚ ድንጋይ ሲወረውሩ ከቤተሰብ ድረሱልን በማለት ስልክ የተደወለላቸው ሚሊሻዎች በፍጥነት ደርሰዋል። በወቅቱም በአቶ ኡመር ይብሬ ቤት ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አውቶማቲክ በማድረግ የተኮሱ ስለመሆናቸው ነው የተገለፀው። ከዛም ሚሊሻዎች ራሳቸውንና የተከበቡ ሴቶችና ህጻናትን ለማዳን ባደረጉት የአፀፋ ምላሽ ነፍሰ ገዳዮቹ ወደ ጫካ መግባታቸው ተገልጧል። ከነበረን አጭር ቆይታ ለመረዳት እንደቻለው በአቶ ኡመር የእጅ ስልክ ላይ በማያውቁት ቁጥር በተደጋጋሚ እንደተደወለላቸውና አድራሻቸውን ይጠይቋቸው እንደነበር፤ ማንነታቸውን ሲጠየቁ ግን ስልኩን ጀሮአቸው ላይ ይዘጉ ነበር። ከአቶ ኡመር ጋር በምንወያይበት ቅጽበትም ከሌላ አቅጣጫ ሌላ የድረሱልኝ ጥሪ መሰማቱን ገልፀው ስልካቸውን ለመዝጋት መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። የሚሊሻ ኮማንደሩ እንደገለፁት አሳሳቢ የሆነው ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብል፣ መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ መብዛቱ ነው። በተለይ ደግሞ የመንግስት ተቋማት የኦነግ ሸኔዎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚደግፉ መሆናቸው ትግሉን አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል። የልዩ ሀይል አባላት ሚሊሻዎችን ለማገዝ ጥረት የሚያደርጉ ቢሆንም በቁጥር ውስን ሆነው እንደሚላኩ ጠቁመዋል። ንፁሃን የአማራ ተወላጆችን እየለዬ እየጨፈጨፈ ያለን ቡድን ስለምን ይደግፉታል? ስንል ለጠየቅናቸው ሲመልሱ ወደፊት አሸንፎ መንግስት ይሆናል የሚል አረዳድ ሳይኖራቸው እንዳልቀረ ተናግረዋል። የመንግስት መዋቅርና ከህዝቡ ድጋፍ የሚሰጡ በርካቶች መኖራቸው የተረጋገጠ ከሆነ እናንተ ሚሊሻዎች ለምታደርጉት ትግል እንቅፋት አይሆንም ወይ ለተባሉት ሚሊሻው ሲመልሱ ያስቸገራቸው ይሄኛው የድብብቆሽ አካሄድ መሆኑን ሳይገልፁ አላለፉም። አቶ ኡመር ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆኑም እያገዙን ነው ይበሉ እንጅ ያነጋገርናቸው በርካታ ምንጮች ልዩ ሀይሉ ከኦነግ ሸኔዎች ጋር ውጊያ ለመግጠም ፍላጎት እንደሌለው፣ በውስጥ የመረጃ ልውውጥ ሁሉ የሚያደርጉ እንዳሉ ነው የጠቆሙት። ከአቢደንጎሮ ወረዳ ኢዶኪሳ ቀበሌ የሚሊሻ ኮማንደር እና ከነዋሪዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply