
ሰበር ዜና! የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል በውልቂጤ ከተማ በንጹሃን ላይ በወሰደው የሀይል እርምጃ የሠው ህይወት ማለፉ ተሰማ! የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በጉራጌ ዞን ወልቄጤ ከተማ “ውሁ ማግኘት አልቻልንም” በሚል ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ ልዩ ኃይል በወሰደው እርምጃ እስካሁን ከ5 በላይ ሰዎች ተገደሉ። በዛሬው ዕለት በወልቄጤ ላለፉት አራት ወራት ውሃ በመጥፋቱ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍም እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች ባዶ ጀሪካን ይዘው ታይተዋል፡፡ የየወልቄጤ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በውሃ እጦት ምክንያት ስራ መስራት አልቻልንም፣ ስራ ብቻ ሳይሆን ለበሽታም እየተጋለጥን ነው በሚል በሰልፍ ወደ መንገድ በወጡ ነዋሪዎች ላይ የደቡብ ክልል ልዩ መለዮ የለበሱ ወታደሮች በወሰዱት የኃይል እርምጃ በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሆስፒታል የገቡ ሲሆን እስካሁን ከአምስት በላይ ሰዎች መገደላቸውን አንድ የከተማው የአይን እማኝ ነዋሪ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። መብታቸው ለመጠየቅ በወጡ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱት እርምጃ ተከትለው አሁን ላይ በከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩንም አስረድቷል። በከተማዋ የሚታየው ንጹ የመጠጥ ውሃ እጦትን በተመለከተ ለሃላፊዎች ብናሳውቅም ችግሩ እንዳልተቀረፈም ሲሉ ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ሰልፉ የተበተነ ቢሆንም ተኩስ ግን እንዳልቆመ ለማረጋገጥ ተችሏል “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post