ሰበር ዜና! የግፍ እስረኞች እነ እስክንድር ነጋ ከእስር ተፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ…

ሰበር ዜና! የግፍ እስረኞች እነ እስክንድር ነጋ ከእስር ተፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በግፍ ከታሰሩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣አስካለ ደምሌ እና ቀለብ ስዩም ላለፉት ሁለት ዓመታት መታሰራቸው መታሰራቸው ይታወቃል። የፍትህ ሂደቱ እንዲሻሻል በእውነተኛ ምስክር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በእስር ቤት ጭምር ሆነው ከፍ ያለ ትግል ሲያደርጉ የነበሩት የባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታህሳስ 29 ቀን 2014 አመሻሹን ከእስር ተለቀዋል። ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር የቀጥታ የስልክ ውይይት ያደረገው ስንታየሁ ቸኮል ከጅምሩ እስራችን ፖለቲካዊ ነበር፤ አሁንም የተፈታነው በፖለቲካ ውሳኔ ነው ብሏል። አስካለ ደምሌ በበኩሏ ከእስር በመፈታታቸው የተሰማትን ደስታ በመግለጽ ድሮም ቢሆን ባልደራስን ለማዳከም ተብሎ እንጅ አንድም ወንጀል እንዳልፈጸሙ እንደሚታወቅ ገልጻለች፤ ከጎናቸው ለነበሩ ወገኖችም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርባለች። ይሁን እንጅ ይህ እስር የበለጠ እንዲበረቱ እንደሚያደርጋቸው በመግለጽ ከንጹሃን ፍጅት በስተጀርባ በወንጀሉ የተሳተፉ አካላት ጉዳይ ግን በህግ ተጣርቶ ተገቢ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ተናግራለች። ቀለብ ስዩም በበኩሏ በምሽት መፍታቱ በራሱ አግባብነት የሌለው አካሄድ ነው ብላ እንደምታስብ ተናግራለች። በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ያልተደሰቱ አካላት ለእስር እንደዳረጓቸው በመግለጽ ከጎናቸው ለነበሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋና አቅርባለች፤ ተፈተናል እንኳን ደስ አላችሁም ብላለች። እነ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ ታህሳስ 29 ቀን 2014 ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ የተፈቱ ሲሆን በርካታ የባልደራስ እና የአመራሮቹ ደጋፊዎችና የፓርቲው አባላት በቃሊቲ እስር ቤት ከበው መፈታታቸውን ሲጠባበቁ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply