You are currently viewing ሰበር ዜና! ፖሊሱ በፋኖ አባላት ተይዟል‼ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በላሊበላ ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሦስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ላይ ጥይት የተኮሰው የትራፊክ…

ሰበር ዜና! ፖሊሱ በፋኖ አባላት ተይዟል‼ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በላሊበላ ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሦስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ላይ ጥይት የተኮሰው የትራፊክ…

ሰበር ዜና! ፖሊሱ በፋኖ አባላት ተይዟል‼ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በላሊበላ ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሦስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ላይ ጥይት የተኮሰው የትራፊክ ፖሊስ አባል በፋኖ አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ:: በላሊበላ ከተማ አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል ትናንት ከሰዓት በኋላ የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሦስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች በስራ ላይ እንዳሉ ተኩሶ ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወሳል። አሽከርካሪዎቹ ወዲያዎኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን በዚህም በከተማዋ ውጥረት ነግሶ አምሽቷል። አሽከርካሪዎቹ ላይ ጥይት ተኩሶ በማቁሰል ተሰውሮ የነበረው የትራፊክ ፖሊስ አባል በአሳምነው ልጆች (በነበልባሎቹ ፋኖዎች) ቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ድምፅ የፋኖ አባላቱን በማነጋገር አረጋግጫለሁ ሲል መረጃውን አጋርቷል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24 የፋኖ አባላቱ ስለከተማዋ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ በቀኑ የዜና ሰዓታችን የምናቀርብ ይሆናል

Source: Link to the Post

Leave a Reply