You are currently viewing ሰበር የእስር ዜና “…ለወራት ከሕዝብ ዕይታ ተሰውሮ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለው እስክንድር ነጋ በጎ…

ሰበር የእስር ዜና “…ለወራት ከሕዝብ ዕይታ ተሰውሮ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለው እስክንድር ነጋ በጎ…

ሰበር የእስር ዜና “…ለወራት ከሕዝብ ዕይታ ተሰውሮ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለው እስክንድር ነጋ በጎጃም ክፍለ ሃገር በቡሬ ከተማ በዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተይዞ ወደ ባህርዳር ከተማ መወሰዱ ተነግሯል። ለምን ከዕይታችን ተሰውረህ ቆየህ? የት ነው ተደብቀህ የነበረው? የሚሉት የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊሶቹ ለጥያቄና ለምርመራ በሚል እንደወሰዱት ነው የተነገረው። “…ከእስክንድር ጋር በቅርብ እንደሚገናኙ መረጃ እንዳለው የማውቀው ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውም ይህንኑ አረጋግጦልኛል። እስክንድርን ዐማሮቹ ይዘው ወደ ባህርዳር እንደወሰዱት የታወቀ ሲሆን በየትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንዳቆዩትም እስከአሁን አለመታወቁንም በስልክ ያነጋገርኩት የእስክንድር የሥራ ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ጌጥ…ዬ ያለው አረጋግጦልኛል። ዐማሮቹ እስክንድርን ለአዲስ አበባው የኦነግና የህወሓት መንግሥት አሳልፈው ይስጡት ወይም በዚያው በባህርዳር ፍርድቤት ያቅርቡት እስከአሁን የታወቀ ነገር የለም። ምንጭ ዘመድኩን በቀለ

Source: Link to the Post

Leave a Reply