You are currently viewing #ሰበር_ዜና ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው የአዲስ ማለዳ ዘገባ አማራ ሚዲያ መእከል ጥር 18 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢ…

#ሰበር_ዜና ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው የአዲስ ማለዳ ዘገባ አማራ ሚዲያ መእከል ጥር 18 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢ…

#ሰበር_ዜና ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው የአዲስ ማለዳ ዘገባ አማራ ሚዲያ መእከል ጥር 18 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኩረጃን ለማስቀረትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚል፣ በልዩ ሁኔታ ከተሰጠው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከ28 ሺሕ እንደማይበልጥ አዲስ ማለዳ ከአስተማማኝ ምንጮቿ ሰማች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲ በተሰጠው ፈተና ከ980 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባውን ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺሕ ገደማ መሆናቸው አዲስ ማለዳ ከትምህርት ሚኒስቴር ምንጮቿ ሰምታለች፡፡ ከፍተኛ ጥያቄ የሚነሳበትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል እና የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ላይ የሚስተዋለውን ኩረጃ ለማስቀረት ወሳኝ ነው የተባለለት ፈተና በጥብቅ ቁጥጠር ከ50 በሚበልጡ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ የፈተና ውጤቱ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በበይነመረብ ይፋ እንደሚደረግ፣ ተማሪዎችም በተሰጣቸው የመለያ ቁጥር ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ በውጤቱ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 130 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው የቅበላ አቅም የ2014 ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ከ20 በመቶ የማይበልጥ ነው ማለት ነው፡፡ ከፍተኛ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ማጋጠሙን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሰሙ ሲሆን፣ ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ምን ይደረግ በሚለው ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በውይይቱ የዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት አቅም ጋር የሚጣጣም ተማሪ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንን ተከትሎ፣ ዩኒቨርስቲዎች በመቀበል አቅማቸው ልክ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ አማራጭ እየተፈለገ ነው፡፡ በዚህም በልዩ ሁኔታ ለማለፊያ የቀረበ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ወስደው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረግ የሚለው አንዱ አማራጭ ሆኖ በመንግሥት በኩል እየታየ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያውቁት የተደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ የ2014 የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ፣ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለውን ስብራት ለማከም እንደ አንድ የመፍትሔ አቅጣጫ ተወስዷል፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግበራዊ የተደረገው የፈተና ስርዓት፣ በዩኒቨርስቲ መምህራን አማካኝነት፣ ተማሪዎችም ከተማሩበት አካባቢ ርቀው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢዎች ውስጥ የተሰጠ ነበር፡፡ ተማሪዎች ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ውጤታቸውን በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot ማየት ይችላሉ፡፡ አዲስ ማለዳ እንደዘገበው

Source: Link to the Post

Leave a Reply