#ሰበር_ዜና ፖለቲከኛው በረከት ስምዖን ከስር ተፈታ! ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ላለፉት ዓመታት በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው በረከት ስምዖን ዛሬ ጥዋ…

#ሰበር_ዜና ፖለቲከኛው በረከት ስምዖን ከስር ተፈታ! ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ላለፉት ዓመታት በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው በረከት ስምዖን ዛሬ ጥዋት ከእስር መፈታቱን የአሻራ ምንጮች አረጋግጠዋል። በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ፖለቲካ በተለይ በኢህአዴግ ዘመን ቆራጭ ፈላጭ ከሚባሉ ጉምቱ ፖለቲከኞች ከሚባሉት ተርታ የሚመደብ ሲሆን ለውጥ መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በእስር መቆየቱ ይታወሳል። በተቃራኒው የአዲሱ ትውልድ ነፀብራቅ የሆነው አርበኛ ዘመነ ካሴ በሴረኞች በእስር ላይ ይገኛል። በከባድ የሙስና ቅሌት የተከሰሰው አቶ በረከት ስምዖን ለአራት ዓመታት በእስር ላይ ቢቆይም የፍትህ ስርዓቱ ሌባን የሚያነግስ በሌላ መልኩ እንደ አርበኛ ዘመነ ካሴ ያሉ ሃቀኛ የህዝብ ልጆች ወደ ወህኒ እንዲወረወሩ በስርዓቱ ተፈርዶባቸዋል ብለዋል የመረጃ ምንጫችን። በረከት ስምዖን በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ኤርፖርት መድረሱንም አረጋግጠናል። ፍትህ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply