You are currently viewing ሰበር!_የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ዝምታውን ሰበረ_”በአባሎቻችን ላይ የሚደረግ ህገ ወጥ አፈና እና ማዋከብ እጅግ አስቆጥቶናል! ትግላችንን እስከ ቀራኒዮ ከፍታ እናስቀጥላለን!” ሲል አቋ…

ሰበር!_የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ዝምታውን ሰበረ_”በአባሎቻችን ላይ የሚደረግ ህገ ወጥ አፈና እና ማዋከብ እጅግ አስቆጥቶናል! ትግላችንን እስከ ቀራኒዮ ከፍታ እናስቀጥላለን!” ሲል አቋ…

ሰበር!_የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ዝምታውን ሰበረ_”በአባሎቻችን ላይ የሚደረግ ህገ ወጥ አፈና እና ማዋከብ እጅግ አስቆጥቶናል! ትግላችንን እስከ ቀራኒዮ ከፍታ እናስቀጥላለን!” ሲል አቋምን አስታውቋል፤ ባለ6 ነጥብ የአቋም መግለጫም አውጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ ሙሉ መግለጫ:_ በህግ ማስከበር ሽፋን ህገወጥ ድርጊቶች ባስቸኳይ ይቁሙ ከጥንት አባቶች እና እናቶች አርበኝነትና የሀገር ፍቅርን በመውረስ ከዘመን ዘመን ወራሪና ጨቋኝ ጠላቶችን እየመከተ ዛሬ ድረስ የዘለቀ የፋኖ አርበኝነት ትግል ባለፉት 30 ዓመታት በአዲሱ ትዉልድ ቅኝ እና አፓርታይዳዊ የትህነግ ቡድንና ተቀጽላዎቹ በሀገራችን ህዝቦችና በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ የደቀኑትን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ አያሌ ጓዶቻችን የህይወትና የአካል መስዋትነት በመክፈል የአባቶቻችንና የህዝባችን አዳራ በፅናት እየተወጣን እንገኛለን፡፡ ባለፉት ዓመታት በተደረገዉ መራር ትግል መለስተኛ ድሎች የተገኙ ቢሆንም ህዝባችን አሁንም ከከፍተኛ የህልዉና ስጋት አልተላቀቀም። በተለይ የአማራ ህዝብ ላይ ማንነትን ኢላማ ያደረጉ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አስተምሮዎችና በጅምላ ጭፍን ጥላቻ ታጅበው በሀገሪቱ ታሪክ ያልታየ እጅግ አሰቃቂ መከራ ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የጠላት ጥቃቶችና ወረራዎች በስሁት ላይ ይገኛል። ይህን የጠላት ጥቃት ለመመከት ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ፣ህዝባችንና ከህዝባችን ወዳጆች ጋር ጥምረት ፈጥረን የጠላትን ጥቃት ለመመከት ባለፉት 2 ዓመታት ትግል ላይ የምንገኝ ይሁን እንጅ በፋኖ አደረጃጀት እና በዓባሎቻችን ላይ ያነጣጠሩ መሰረተ ቢስ የስም ማጥፋትን ጨምሮ ዓባሎቻችን የማፈን ፤የመግደል ፣ የማሳደድ እና የማዋከብ በመንግስት እየተፈፀመብን ሀገራችን ከገጠማት አደጋ አንፃር በሆደ ሰፊነትና በዉይይት ለመፍታት ጥረት እያደረግን ቆይተናል። በቅርቡ ሶስት ወራት ዉስጥ በህግ ማስከበር ሽፋን የሚደረገው ህገወጥ ጫናና ጥቃት ድርጅታችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ክፉኛ እያስቆጣ ሲሆን ህዝባችን ደባዉን እስኪረዳ ህግን መሰረት ያደረገ ቁመናን መርጠን ቆይተናል። በሒደቱም በተከፈተብን መሰረተ ቢስ ፕሮፖጋንዳ ልክ በህግ አግባብ ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት አንድም ዓባል ባይኖርም አፈናዉና ማሳደዱ አሁንም በዓባሎቻችን ላይ ቀጥሏል፡፡ በህዝባችን ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት (etic cleaning) እና ማፈናቀል ፣ ዝርፊያና ወረራም ጠላት የገፋበት በመሆኑ የወገናችን እልቂት ከቁም ነገር የማይቆጠርበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። በህግ ማስከበር ሰበብ ዓባሎቻችን የህይወት መስዕዋትነትን ጨምሮ ለእስር እና ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን በህግ ሽፋን በቁጥጥር ስር ውለው በህግ አግባብ በፍ/ቤት ነፃ የተባሉ እና በዋስ እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው ዓባሎቻችን ህግን በመተላለፍ በሃይል አፍኖ የማዛወርና ከህግ በላይ አስሮ የማንገላታት በደሎች እየደረሱብን ይገኛል። ለአብነትም ሰኔ 20/2014 ዓ/ም በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር በግልፅ በሰላማዊ ሁኔታ በወለጋ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችን ፣ የሱዳን ወራሪ ሃይል በምዕራብ ጎንደር ዞንና በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ በኩል የሀገራችን ወሰን ዘልቆ በመግባት እየፈፀመ የሚገኘዉን ወረራና ዝርፊያ በተመለከተ እንዲሁም የትህነግ ጥቃትን ለመቀልበስ ከአራቱም የአማራ ግዛቶች የተወጣጡ የፋኖ ዓባላት ከክልሉ መንግስት ጋር ለመነጋገር ወደ ባህርዳር አቅንተው ባረፉበት ሆቴል በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑ ይታወቃል። ምርመራው በፌደራል ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ሲደረግ ቆይቶ ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተሰጠው ውክልና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ክሳቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ሀምሌ 22/2014 በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው በ25 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍ/ቤቱ በወሰነው መሰረት ሁሉም ዓባሎቻችን ገንዘቡን ከፍለው የመፍቻ ትዕዛዝ ለባህርዳር ማረሚያ ቤት ደርሶ ሊፈቱ ሲዘጋጅ በህግ ማስከበር ሽፋን አስሮ በህግ የተፈቱ ዓባሎቻችን የህግና የህገ መንግስት መብቶቻቸውን በመተላለፍ አፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ለመውሰድ በመሞከሩ ህግ ይከበር ባሉ ወገኖች ርብርብ ለጊዜው ታፍነዉ ወደሌላ ቦታ ባይወስዱም ያለምንም የህግ አግባብ አሁንም በባህርዳር ማረሚያ ቤት ይገኛሉ። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ዓባል የሆነው ፋኖ አንተነህ ድረስ በተመሳሳይ በፍ/ቤት ትዕዛዝ የዋስትና ገንዘብ አሲዞ የመፍቻ ትዕዛዝ ለማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤት የተሰጠ ቢሆንም ከህግ አግባብ ውጭ በመንግስት ሰራዊት ወደሌላ ቦታ ተዛውሮ በእስር ሲንገላታ ከቆየ በኋላ ፍ/ቤቱ በድጋሜ በሰጠዉ ትዕዛዝ በቅርቡ ከእስር መፈታቱ ተጠቃሽ በህግ ማስከበር ስም በዓባሎቻችን ላይ የደረሱ የህግጥስቶች ናቸዉ። ለሀገር ህዝብ ጥቅምና ደህንነት በራሳችን ፍፁም ፍላጎትና ትጥቅና ስንቅ መስዕዋትነት በመክፈል ላይ የሚገኘው ዓባሎቻችን ላይ የሚደረገው ህገወጥ አፈናና ማዋከብ እጅግ ያስቆጣን መሆኑን እየገለጽን ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሁነን ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ከፍታ እናስቀጥላለን። ስለሆነም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሚከተሉት ጉዳዮች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ያሳስባል:_ 1ኛ- በባህርዳር ማረሚያ ቤት የፍ/ቤት መፍቻ ትዕዛዝ የደረሳቸዉ ዓባሎቻችን የሚመለከተው አካል ህግን አክብሮ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈታቸው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ያሳስባል። 2ኛ_በተመሳሳይ ከህግ አግባብ ውጭ በተለያዩ ቦታዎች ታስረው የሚገኙ የአማራ ፋኖ ዓባሎችና ንቁ የህዝባችን ታጋዮች አስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጣቸውና አፍኖ ወደሌላ ቦታ ለማዛወር የሚደረገውን ህገወጥ መከራ ቅንጣት የማንታገስ መሆኑን እንገልፃለን። 3ኛ- በጠላት ናፋቂ የውስጥ ሸማቂዎች ሴራ እየተሳደዱ የሚገኙ ፋኖዎቻችን እኩይ ድርጊት እንዲገታ እያሳሰብን በህገወጥነት ዓባሎቻችን ላይ የሚደርሰው ህገወጥ ድርጊት የማይቆም ከሆነ ህግ እንዲከበር ማንኛውንም ትግል በአፋጣኝ ለመጀመር የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እንደሚገደድ እናሳውቃለን። 4ኛ -በጠላት ወረራ ስር የሚገኙ የአማራና አፋር ወረዳዎችን ከወራሪ ነፃ ለማውጣት ቁርጠኛ መሆናችን እየገለፅን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ የአማራ ማንነት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ያሳስባል። 5ኛ_ይደረጋል በተባለዉ የሰላም ድርድር የሀገራችን ህዝቦችና የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥቅምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ስህተት እንዳይፈፀም እናሳውቃለን፡፡ 6ኛ_በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የአማራ ተወላጆች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ጭፍጨፋ በጥብቅ እናወግዛለን በድርጊቱ የተሳተፉ እና ሃላፊነታቸውን ያልተወው ምቹ ሁኔታ የፈጠሩ አካሎች ዘላለማዊ እዳ በትክሻችሁ ያረፈ መሆኑን እናስገነዝባለን። ውድ የሀገራችን ልጆች ፍትህናርዕትህ የምትመኙ ሁሉ በወገናችንና በዓባሎቻችን ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ህገወጥነት በጋራ ለማስተካከል ከጎናችን እንድትቆሙ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በፈሰሰው ደማችንና በከሰከስነው አጥንታችን ስም ጥሪ እናደርጋለን። የተዘረዘሩት ጥያቄዎቻችን በአስቸኳይ የማይፈቱ ከሆነ በቀጣይ ዝርዝር ህዝባዊ ትግል ለማስጀመር የምናውጅ ሲሆን በንቃት እንድንጠባበት የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ይገልፃል። አንድነት ሀይል ነዉ! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደር አማራ/ኢትዮጵያ_ ሀምሌ 25/2014 ዓ/ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply