ሰባት ቅርሶች ከእንግሊዝ ተመልሰዋል፡፡

በመቅደላ ጦርነት ከሃገር ተዘርፈው የተወሰዱ ሰባት ቅርሶች ከእንግሊዝ ሃገር ተመልሰዋል ተብሏል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደተመላከተው በመቀደላ ጦርነት ከሃገር ተዘርፈው የተወሰዱ ሰባት ቅርሶች ከእንግሊዝ ሃገር እንዲመለሱ መደረጉ ተጠቆመ።

የቱሪዝም ሚንስትር ሚንስቴሯ አምባሳደር ናሲሴ እና ሌሎች የሚኒስትሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ባለፉት 9 ወራት በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች መመዝገባቸው የተገለፀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አምስት መቶ ቅርሶች በተሟላ መረጃ በዲጂታል ዳታ ቤዝ መስነዱን ተገልጻል፡፡

እንዲሁም አንድ ሽህ አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ቋሚ ቅርሶች መመዝገባቸውን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች በዲፕሎማሲ እና በውይይት የማስመለሱ እንቅስቃሴ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply