ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም ይሰጥ የነበረው የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና በዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት መቀየሩን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3/2016 እስከ ሰኔ 10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማውጣቱን ገልጿል። ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በመኾኑ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ወደ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም መዛዎሩን ነው የገለጸው። ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply