You are currently viewing “ሰዉ ለመብቱ መከራከር ወይም ጠላቱን መርታት ቢያቅተዉ እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል?”  የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ከተናገረው_በሸንቁጥ አየለ  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ሰዉ ለመብቱ መከራከር ወይም ጠላቱን መርታት ቢያቅተዉ እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል?” የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ከተናገረው_በሸንቁጥ አየለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ሰዉ ለመብቱ መከራከር ወይም ጠላቱን መርታት ቢያቅተዉ እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል?” የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ከተናገረው_በሸንቁጥ አየለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወያኔ ነገደ አማራን መጨፍጨፍ እና ማፈናቀል የጀመረዉ ከወልቃይት፣ ራያ ከዚያም መተከል ጀምሮ ነዉ። በኦነግ ተባባሪነት እና አስተባባሪነት ደግሞ በወለጋ፣ አርሲ፣ ሀረር እና በብዙ ቦታዎች ነዉ። በወቅቱ ይሄን የወያኔን ነገደ አማራ ጭፍጨፋና ማፈናቀል ፊት ለፊት ተቃዉመዉ የገጠሙት የመላዉ አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) መስራች ፕሮፌሰር አስራት በስራቸዉ ብዙ ጀግኖች አፍርተዉ ነበር። ከነዚህ ወጣት ጀግኖች መሃል በወቅቱ ገና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ድርግሪዉን እየሰራ የነበረዉ እና በአሁኑ ሰዓት የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር የሆነዉ ማሙሸት አማረ አንዱ ነበር። ማሙሸት አማረ በዚያን ወቅት በነገድ ማንነቱ ይጨፈጨፍ የነበረዉ አማራ ባህሪ በጣም ያስገርመዉ ፣ያበሳጨዉ እና ብዙ አስገራሚ ንግግሮችንም ያናግረዉ እንደነበረ ተመዝግቦ ተይዞለታል። ነገዱ የሚጨፈጨፍበት የአማራ ህዝብ መአህዶችን ሲያይ ግማሹ ይሸሻቸዉ ነበር፤ ግማሹም ፊቱን አኮሳትሮ ያልፍ ነበር። ገላምጧቸዉም ያልፍ ነበር። በአማራ ነገድ ስም ተደራጅታችሁ የወያኔን አጀንዳ ግቡን እንዲመታ ልታደርጉ ነዉ ብሎ ይፎክርባቸዉ ወይም አምርሮ ይከራከራቸዉ ነበር። ገጠመኝ:_ ማሙሸት አማረን አንድ የሚያዉቀዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ አንድ ቀን ወደ አንድ ምግብ ቤት ከጓደኞቹ ጋር ምሳ ሊበሉ ሲገቡ ያዬዋል፤ ያ ሠዉ ታዲያ ገና ምግቡን ሳይጨርሰዉ፣ ወዳፉ ያለዉን ዉሃም ሳይጠጣዉ እነ ማሙሸትን ሲያይ በፍጥነት ተስፈንትሮ በመነሳት ሂሳብ ከፍሎ ሊወጣ ሲንደረደር ማሙሸት ያስተዉለዋል። ማሙሸት በባህሪዉ አንድ ነገር ከያዘ እስከ መጨረሻዉ ሳያጣራ አይተዉምና ሰዉዬዉን ከተል ብሎ ክንዱን ይይዘዋል። ክንዱንም ይዞ ስለሚተዋወቁም ጭምር “እንዴት ነህ ወንድሜ? ምኔዉ በጣም ተጣደፍክ? በሰላም አይደል እንዴ?” ይለዋል። ሰዉዬዉ በጣም ተበሳጨ፤ ተቆጣ። “ልቀቀኝ፣ አትንካኝ። ከናንተ ጋር መነካካት አልፈልም። ከናንተ ጋር መታዬትም መነጋገርም አልፈልግም” ይለዋል። ማሙሸት አማረም “ምነዉ ወንድሜ? ያስቀዬምኩህ ነገር አለ እንዴ? ምን በድዬህ ነዉ?” ይለዋል። ሰዉዬውም እንደ እብድ እየጮህ “እናንተ መአህዶች ናችሁ። እናንተ የመንግስት ጠላት ናችሁ። ሁለተኛ አጠገቤ እንዳትደርስ። አትድረስብኝ። እኔም አልደርስብህም። እኔ የባንክ ሰራተኛ ነኝ። እኔ የተከበርኩ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ። ከናንተ ጋር ንክክኪ አልፈልግም” ይለዋል። ማሙሸት አማረ ልምድ ሆኖበት ይመስላል የሰዉ ነገር ሲገርመዉ አንድ ቃል ብቻ “ሆይ” ብሎ ዝም ይላል። “ሆይ” አባባሉ ግን በጣም አጥንት ድረስ የሚገባ መልዕክት ያስተላልፋል። እናም ስድስት ወር ሳይሞላዉ ወያኔ የባንክ ሰራተኞችን ጥርግ አድርጎ ከንድግ ባንክ ማባረር ጀመረ። በዋናነትም ነገደ አማራ የሆኑትን የባንክ ሰራተኞች በወረንጦ ለቅሞ አባረራቸዉ። ገራሚዉ ክስተት:_ አስገራሚዉ ነገር የሚጀምረዉ ታዲያ እዚህ ጋ ነዉ። በመጀመሪያ ከተባረሩት ሰዎች ባለፈዉ እነ ማሙሸትን ሲያይ ከመአህዶች ጋር ንግግርም ንክኪም አልፈልግም ብሎ ከምግብ ቤት ፈርጥጦ ሲወጣ የነበረ ሰዉ ሆነ። እናም አንድ ቀን ማሙሸት አማረ ከወዳጆቹ ጋር ቱሪስት ሆቴል ጠዋት ላይ ተሰብስበዉ የሀገር ጉዳይ እየመከሩ እያለ ያ ባለፈዉ ከመአህዶች ጋር ንግግርም ንክኪም አልፈልግም ብሎ ከምግብ ቤት ፈርጥጦ ሲወጣ የነበረ ሰዉ ወደ ማሙሸት አማረ እየተንደረደረ መጣ። እናም የደረሰበትን በደል ዘርዝሮ ለማሙሸት አማረ መናገር ጀመረ። “ይሄዉ እኛን አማሮቹን ለይተዉ እና ለቅመዉ ከንግድ ባንክ አባረሩን። ዘራችን ተለይቶ ነዉ የተባረርነዉ” ሲል ከመአህዶች ጋር ንግግርም ንክኪም አልፈልግም ብሎ ከምግብ ቤት ፈርጥጦ ሲወጣ የነበረ ሰዉ ለማሙሸት የሆነበትን ማብራራት ጀመረ። ማሙሸት አማረ ጥያቄ መጠዬቅ ጀመረ። “እና አሁን ይሄን ለምንድን ነዉ ለኔ የምትነግረኝ?” ሰዉዬዉ ይመልሳል። “የደረሰብንን ዘርዝራችሁ ለሚዲያዎች እንድታደርሱልን እንዲሁም ለመንግስት አቤቱታችንን እንድታቀርቡልን ነዋ” ይለዋል ከመአህዶች ጋር ንግግርም ንክኪም አልፈልግም ብሎ ከምግብ ቤት ፈርጥጦ ሲወጣ የነበረዉ ሰዉ። ማሙሸት ያችን ምትሃተኛ አባባሉን አሁንም ደግሞ ተናገራት። “ሆይ” አለ። ከዚያ ዝም አለ። ሰዉዬዉ ግን መለፍለፉን እና ብሶቱን መናገሩን ቀጠለ። ብዙ ካዳመጠ ብኋላ ማሙሸት “በል አሁን የተናገርከዉን ሰምተናል። እኛ ያንተን ጉዳይ ይዘን አንተ መንግስት ለምትለዉ አቤት ስንል አንገኝም። አንተ ለራስህ ለመከራከር ብቁ ነህ። እኛ መጀመሪያ መንግስት አለ ብለን አናምንም። ለሌለ መንግስት ነዉ አንተ አቤቱታዬን አቅርቡልኝ የምትለዉ። እኛ በየአቅጣጫዉ እየተጨፈጨፈ ያለዉን የአማራን ህዝብ ሞት ለማስቆም፣ የህዝብን ነጻነት ለማስመለስ እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማረጋገጥ እየታገል ያለን ሰዎች ነን።” ማሙሸት ቆምጨጭ ብሎ ለሰዉዬዉ መለሰለት። ሰዉዬው ለመሄድ ተነሳ። ወደ ፊት አንድ ሁለት እርምጃ መራመድ ጀመረ። በዚህ መሃል ማሙሸት አማረ አብረዉት ላሉት ጓደኞቹ መናገር ጀመረ። ሰዬዉም ድንገት መሃል ላይ ቀጥ ብሎ የማሙሸትን ንግግር ማድመጥ ጀመረ። ማሙሸት መናገሩን ቀጠል:_ “ሆይ..” “ይሄ ሰዉዬ እኮ አሁንም መንግስት በድሎትም አላኮረፈም። መንግስትን እየተለማመጠ እኮ ነዉ። ሰዉ ተበድሎ፣ በዘሩ ተገፍቶ፣ ከስራ ተፈናቅሎ ከመኖሪያ ቀዬዉ ተፈናቅሎ፣ በነገዱ ተገሎ እንዴት ቢያንስ አያኮርፍም። ሰዉ ለመብቱ መከራከር ወይም ጠላቱን መርታት ቢያቅተዉ እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል? አሁን እየተገደለ እና እየተፈናቀለ ያለዉ አማራም የሚያሳዬዉ ባህሪ እኮ እንደዚህ ሰዉ አይነት ነዉ። ወያኔ እየገደለዉ እና እያፈናቀለዉ መንግስት ይድረስልኝ ብሎ ይጮሃል። ይሄም ሰዉዬ ወያኔ ዘሩን ቆጥሮ አባሮት መንግስት ይድረስልኝ፤ መንግስት ጉዳዬን ይይልኝ ይላል። ሆይ…” ማሙሸት አማረ ንግግሩን ቀጥሏል። ከመአህዶች ጋር ንግግርም ንክኪም አልፈልግም ሲል የነበረዉ እና ሲቸግረዉ ደግሞ መአህዶች ለመንግስት አቤት ይበሉልኝ ያለዉ ስዉዬ ወንገር ወንገር እያለ ሄደ። አሁንም በመላዉ ኢትዮጵያ የሚጨፈጨፈዉ ነገደ አማራ ጉዳዩ ተመሳሳይ ጥያቄ ያስነሳል። ሰዉ ቢያንስ ግን እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል? እንዴት ነገደ አማራ በጠላቶቹ ላይ 30 አመታት ሙሉ ማኩረፍ ያቅተዋል? እንዴት ሰዉ ወገኖቹን ከሚያሳርዱት ጋር በአንድ መዐድ ቀርቦ የዘመዶቹን ደም በእንጀራ እየለወሰ ይበላል? በትንሹ ዘሩን እና ነገዱን በሚያሳርዱት ላይ እንዴት ሰዉ ማኩረፍ ያቅተዋል? እንዴት ሰዉ ዘሩን እና ነገዱን ለሚያሳርዱ ጠላቶች ተላላኪ ሆኖ ይሰለፋል? እንዴት እየተገፋና እየተጠቃ ያለ ሰዉ በትንሹ ማኩረፍ ያቅተዋል? እንዴት ሰዉ ወገኖቹ እየታረዱ ለወገኖቹ ድምጽ ከመሆን ይልቅ አልባሌ ጉዳይ ላይ ጊዜዉን ያጠፋል? እንዴት ሰዉ በዘሩ የተነሳ ነገ እንደሚታረድ እያወቀ ቢያንስ እንዴት ማኩረፍ ያቅተዋል? እዉነትም “ሆይ ..” የሚያስብል ጉዳይ ነዉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply