ሰውሰራሽ የመተንፈሻ እጥረትን ለመቅረፍ 180 መካኒካል ቬንቲሌተሮች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ለህክምና ተቋማት እየተሰራጩ ነው ሲል ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ሰው ሰራስ መተንፈሻና ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ይታወቃል፡፡እጥረቱን ለመቅረፍ በቀን 2 ሺ ሲሊንደሮችን የመሙላት ስራ እየተሰራ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ ኃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ ለአሐዱ ገልጻል፡፡

ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ዋጋው ውድ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ሚዛን በቅርቡ 180 የሚሆኑ መካኒካል ቬንትሌተር ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለህክምና ተቋማት የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው ብለው ነገር ግን በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሣሪያ ፍላጎቱን አያሟላም ብለዋል፡፡

ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እየተጠቀሙ የሚተርፉት ከ10 በመቶ የዘለሉ አይደለም ያሉት አስተባባሪው ዋናው ተግባር በሽታውን መከላከል ላይ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ቀን 30/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post ሰውሰራሽ የመተንፈሻ እጥረትን ለመቅረፍ 180 መካኒካል ቬንቲሌተሮች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ለህክምና ተቋማት እየተሰራጩ ነው ሲል ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply