ሰውን በማሰር የሚረኩ የመንግስት አካላት አስተውለው በግፍ የታሰሩትን ፋኖዎች እንዲፈቱ ሲሉ አርበኛ ባዬ ቀናው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም…

ሰውን በማሰር የሚረኩ የመንግስት አካላት አስተውለው በግፍ የታሰሩትን ፋኖዎች እንዲፈቱ ሲሉ አርበኛ ባዬ ቀናው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ትግላቸው በዋናነት በ2008 ዓ.ም የጀመረ መሆኑን የጠቀሱት አርበኛ ባዬ ቀናው አገር አፍራሽ በሆነው ቡድን ማንነታችንናወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ እርስታችን ተነጥቀን ላለፉት በርካታ ዓመታት ስንሰቃይ ቆይታናል ብለዋል። ከሃዲው ትሕነግ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረጉትን ጥቃት ተከትሎ የአማራ ፋኖ በሀገሩ ጉዳይ የማይደራደር በመሆኑ ከአማራ ልዩ ሀይል፣ሚሊሻና መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ የቡድኑን ምሽግ በመደርመስ፤ ለዘመናት የአበጠውን እብሪት በማስተንፈስና በመደምሰስ የራሱን አሻራ አስቀምጧል። እነ አርበኛ ቀናው ባዬም ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከንጋቱ 11:30 ላይ ከወገራ ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ ተነስተው ከአማራ ልዩ ሀይል እና ከሚሊሻው ጋር በመሰለፍ ትሕነግ ሲገነባው የከረመውን የማይለሃምን ምሽግ በመደርመስ ካስለቀቁት መካከል አንዱ ስለመሆኑ አስታውቋል። ማንነታችንና እርስታችንን ያጣንበት ለአገራችን ስንል በመሆኑ መከላከያ ሲነካ ዝም ብለን አናይም በሚል ነው አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል ለዘመናት ታፍነው የኖሩትን የማይጠብሪና የማይለሃም ነዋሪዎች ነጻ እንዲወጡ የተደረገው ብለዋል። ትግሉ ተጀመረ እንጅ አልቋል አንልም ያሉት አርበኛ ቀናው ሰውን በማሰር የሚረኩ አካላት በአማራ ላይ እየሆነ ያለውን ቆም ብለው አስተውለው በግፍ የታሰሩትን ፋኖዎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል። እነ ፋኖ ሰለሞን አጠናው፣ፋኖ ቻላቸው እንየው፣ ፋኖ ብርሃኑ ነጋና ሌሎችም ተፈተው ህዝብን ቢያገለግሉ ጥሩ ስለመሆኑ የገለፁት አርበኛ ባዬ እባካችሁ የአማራ ክልል መንግስት አመራሮች ወገንን በመግደል፣በማሰርና በማሳደድ ስልጣን ያገኙና በተለመደው የሕወሓት መንገድ የሚቀጥሉትን ጅንታዎች በመገምገም ችግሮችን ቅረፉ ሲሉ ተማፅነዋል። አርበኛ ባዬ ሲቀጥሉ ተበታትነን እስካሁን አይተነዋል፤ በዚህም ነውጥ እንጅ ለውጥ አላየነም፤ አሁን ግን በአንድ ስንሰለፍ በጠላት ላይ ምን ያህል ድል እንደተቀዳጀን ይታወቃል ብለዋል። ፋኖ ማለት ለማንነቱ፣ለእርስቱ፣ለሀገሩና ለወገኑ የሚታገል አማራ ነው፤ ያሉት ፋኖ ባዬ ነጻ የወጡ ቀጠናዎችን ከሰርጎ ገቦች ለማፅዳት ሁሌም ዝግጁ ነን ብለዋል። ይሁን እንጅ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተዉ፤ እረፉ የሚሉን አንዳንድ አካላት፣ ትሕነግና ግልገሎቹ እንደገና እንዲንሰራሩና በህዝብ ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ እድል እየሰጡ ነው፤ ይህ ደግሞ ዋጋ ስለሚያስከፍል ቢታሰብበት ጥሩ ነው ሲሉ መክረዋል። በመጨረሻም አገር አፍራሾች እና ነፍሰ ገዳዮች ሱዳንም ገቡ የትም በህግ የሚጠየቁበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ፤ ህዝቡም ሆነ መንግስት ነቅተው አካባቢን ብሎም አገርን እንዲጠብቁ አሳስበዋል። ከአርበኛ ባዬ ቀናው ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply