ሰው በማገት 200ሺህ ብር የተቀበለው ግለሰብ የ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም           አዲስ አበባ ሸዋ የጣቁሣ ወረ…

ሰው በማገት 200ሺህ ብር የተቀበለው ግለሰብ የ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጣቁሣ ወረ…

ሰው በማገት 200ሺህ ብር የተቀበለው ግለሰብ የ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጣቁሣ ወረዳ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አንደበት አዛናው ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 በወረዳው ሮቢት አይብጋ ቀበሌ ልዩ ቦታው ደኑ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ላይ ነበር የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው፡፡ የግል ተበዳይ የሆነውን ሊቀ ጉባኤ አስካለ ካሳሁንን ከጎንደር ከተማ ወደ አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ ለስራ በመሄድ ላይ ሳለ ከመኪና በማስወረድ ጠልፎ መውሰዱን አዲስ ዘይቤ ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡ የወረዳው ዐቃቤ ሕግም የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ‹‹ሰዉን መጥለፍ›› አንቀጽ 586 እና 590(2) (ሐ) ን በመጥቀስ በወረዳው ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ ተከሳሹ ተበዳዩን ከጠለፈ በኋላ 200,000 ብር መቀበሉንም አቃቤ ህግ በክሱ ያካተተ ሲሆን ይህንንም በማስረጃ አስደግፎ አቅርቧል፡፡ መዝገቡን ሲመረምር የቆየው ችሎቱም በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ስለመበየኑ የአዲስ ዘይቤ ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply