ሱር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በጠገዴ ወረዳ ለመንገድ ስራ ሲጠቀምበት ለቆየው የድንጋይና የጠጠር ግብር ከእነ ወለዱ በፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲከፍል ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

ሱር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በጠገዴ ወረዳ ለመንገድ ስራ ሲጠቀምበት ለቆየው የድንጋይና የጠጠር ግብር ከእነ ወለዱ በፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲከፍል ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሱር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በጠገዴ ወረዳ አዲስ ዓለም ቀበሌ ልዩ ስሙ አየር ማረፊያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ ለመንገድ ስራ ግብዓትነት ሲጠቀምበት ለነበረው የድንጋይና ጠጠር ግብር (የሮያሊቲ ክፍያ)በባለሙያ ተጠንቶ 4,727,700 ብር ለወረዳው እንዲከፍል ቢጠየቅም በወቅቱ መክፈል የሚገባውን ሳይከፍል ቆይቷል። የጠገዴ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ባለሙያዎች ከድርጅቱ ፅ/ቤት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድና የባንክ አካውንቱ እንዲዘጋ አድርገዋል። በወቅቱ ባለመክፈሉ የቅጣትና ወለድ 349,577ብር ከ69ሳንቲም በድምሩ 5,077,277ብር ከ 69 ሳንቲም ለወረዳው እንዲከፍል መደረጉን በጠገዴ ወረዳ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ክትትል ዋና የስራ ሂደትአስተባባሪ የሆኑት አቶ መንግስቴ እሸቴ ተናግረዋል። ግብር መግፈል የዜግነት ግዴታ መሆኑን በመረዳት ማንኛውም አካል የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱና በትክክል መክፈል እንዳለበት አቶ መንግስቴ አሳስበዋል ሲል የጠገዴ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply