ሱር ኮንስትራክሽን ከመንገድ ስራ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደ ነበረ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም           አዲስ አበባ ሸዋ ሱር ኮንስትራክሽን…

ሱር ኮንስትራክሽን ከመንገድ ስራ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደ ነበረ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሱር ኮንስትራክሽን…

ሱር ኮንስትራክሽን ከመንገድ ስራ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደ ነበረ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሱር ኮንስትራክሽን የተሰጠውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ትቶ ወደ ምሽግ ቁፈራ ገብቶ እንደነበረ ተገልጧል። በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የበርገሌ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ካሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ሱር ኮንስትራክሽን በክልሉ በኮንትራት ከያዘው የመንገድ ሥራ ወጥቶ በምሽግ ቁፈራ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነበረ። በርገሌ ወረዳ አቅራቢያ የተቆፈረው ምሽግ እስከ 10 ኪሎሜትር እርዝመት 2 ሜትር ጥልቀት 4-5 ሜትር ስፋት እንዳለውና መኪኖች ገብተው መውጣት የሚችሉበት እንደነበረ ገልፀዋል። መከላከያ ሰራዊት ባካሄደው የህግ ማስከበር እርምጃ ከሁለት ሳምንት በፊት በአጭር ሰዓት ምሽጉን ተቆጣጥሮ የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ መንደራቸው እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ካሴ ገልፀዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply