ሱዳንና ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ለማድረግ ቢሞክሩም ለግድቡ የሚደረገው ገቢ ማሰባሰቡ ግን እንደቀጠለ ተገለፀ፡፡

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተፈጠረውን ውጥረት ወደጎን በማለት ከኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 21 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መደረጉን ጽ/ቤቱ አስታወቀ፡፡በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አስፈላጊነት ላይ ከህብረተሰቡ ጋር የተፈጠረውን መግባባት በማጠናከርና የተቀዛቀዘው የግድቡ ድጋፍ እንደ አዲስ ከፍተኛ ገቢ መሰብሰቡን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሐይሉ አብርሃ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የታላቁን  የህዳሴ ግድብ መገንባቷን ተከትሎ የታችኛው ተፋሰስ ሐገራት  ግብፅ እና ሱዳን ግድቡ የወንዙን የውሃ ፍሰት ይቀንሳል በሚል እስካሁን መስማማት አለመቻላቸው ይነገራል፡፡ይሁን እንጅ በከፍተኛ ሁኔታ የሐገሪቱን የኤለክትሪክ ሐይል ያመነጫል የተባለው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ጎን የነበረችው ሱዳን ሐሳቧን በመቀየር ከግብጽ ጎን ከመቆም አልፋ ወረራ መፈጸሟ ይታወቃል፡፡

ሱዳን ሆነ ግብጽ የተለያዩ ተጽኖዎችን ቢያደርጉም የህዳሴው ግንባታው ሁለተኛ ሙሌቱን እንደሚጀምር አቶ ሐይሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

*************************************************************************************

ቀን 20/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ሱዳንና ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ለማድረግ ቢሞክሩም ለግድቡ የሚደረገው ገቢ ማሰባሰቡ ግን እንደቀጠለ ተገለፀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply