
ሱዳን እየተጠናቀቀ ባለው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ተናገሩ። ሊቀመንበሩ ይህንን ማለታቸው የተገለጸው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በካርቱም ያደረጉትን የአንድ ቀን ጉብኝት ተከትሎ ምክር ቤታቸው ባወጣው መግለጫ ነው። ሁለቱ መሪዎች በአገሮቻቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል።
Source: Link to the Post