ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ያዘች አሻራ ሚዲያ ህዳር 21/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር በምትገኘው…

ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ያዘች አሻራ ሚዲያ ህዳር 21/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር በምትገኘው ከሰላ ግዛት አከባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ መያዟን አስታውቃለች። በሱዳን በግዛቷ ያተያዙት በርካታ የተለያዩ የጦር መሰሪያዎች ጠብመንጃ እና የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ጥይቶች ናቸው ተብሏል። የሀገሪቱ በፀጥታ ኃይሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዝ የቻሉት ከኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በኩል ወደ ሱዳን በሚያገናኘው ድንበር አከባቢ ሰሞኑን በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን የሱዳኑ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል። ከሰላ ግዛት የሚገኘው የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች አከባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ህገወጥ የጦር መሳሪያዎቸ ለመቆጣጠር ሁሌም በተጠንቀቅ እንደሚገኝ የግዛቷ የፖሊስ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ካሊድ አዋድ ቦሱፍ ተናግረዋል። ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply