ሱዳን በከሰላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

ሱዳን በከሰላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

አዲስ አባበ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በከሰላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን አስታወቀች።
የግዛቷ አስተዳዳሪ ፈታህ አል ራሀማን አል አሚን እንዳስታወቁት ከዛሬ ጀምሮ ሱዳንን ከኢትዮጵያ የሚያዋስነውን የከሰላን ድንበር በመዝጋት በአካባቢው ያለው ጥበቃ በፀጥታ ኃይሉ ተጠናክሯል።
ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግስት በሕወሐት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከግምት በማስገባት መሆኑንም የአል ሱዳኒ ዘገባ ያመላክታል።
በአካባቢው ያለው የፀጥታ ኃይል ድንበሩን በንቃት እንዲጠብቅና ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የጦር መሳርያ ይዞ ወደ ሱዳን እንዳይገባ እንዲያደርግ መታዘዙንም ተናግረዋል።
በድንበሩ አቅራቢያ ባለችው ዋድ አል ሄሊኦ ያለው ኃይል ሁኔታዎችን በደንብ እንዲያጠና መታዘዙንም አስረድተዋል።
በአንጻሩ ጥገኝነት ፈልገው ወደ ሱዳን የሚመጡ ንፁሃንን ለመቀበል ይህን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ትዕዛዞች እንዲፈፀሙ ይረዳ ዘንድ ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ተቋቁሟልም ነው ያሉት።

The post ሱዳን በከሰላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply