ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ ተጠየቀ

ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና  የአፍሪካ ህብረት አሳሰቡ።

የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ህብረት በጥምረት በሱዳን ዳርፉር ያሰማሩት ሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ መጠናቀቁ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት እና የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋራ ባወጡት መግለጫ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ (ዩናሚድ) በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ደህንነቱ እና ስርዓቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲወጣ የሱዳን አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት እና አንቶኒዮ ጉቴሬዝ  በአካባቢው የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እና ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የተዘጋጀውን ብሄራዊ የተግባር አቅድ ለማስፈፀም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን እንደገለፁ ፒፕልስ ዴይሊ ዘግቧል።

የሰላም አስከባሪ ኃይሉ (ዩናሚድ) ወታደሮች እና የፖሊስ ክፍል ከዛሬ ጀምሮ ዳርፉርን ለቆ ለመውጣት የሚያስችሉ ስራዎች ላይ እንደሚያተኩር ነው የተነገረው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ሱዳን በዳርፉር ያለውን የሰላም ማስከበር ሀይል ደህንነቱና ስርዓቱ ተጠብቆ እንዲወጣ እንድታደርግ ተጠየቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply