ሱዳን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ተቋም እከሳለሁ ማለቷ አስነዋሪ ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አባሳደር ዲና ሙፍቲ ሱዳን ቤንሻንጉል ጉሙዝ የእኔ ነው ማለቷና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ተቋማት
እከሳለሁ ማለቷ አስነዋሪ ነው ሲሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግሯል።

ሱዳን ካላግባብ የተለጠጡ ፍላጎቶች አሏት ያሉት አምባሳደሩ የሱዳን ወታደር መሬት መውረሩ እየታወቀ
ይህም ወታደር አርሶአደሩን ከእርሻው ማፈናቀሉ እየታወቀ ኢትዮጵያን ለመክሰስ መነሳት አስነዋሪ ነው ብለዋል።

የሱዳን አቋም የተምታታ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የውሃና መስኖ ሚኒስትር
የሚሰጡት መግለጫ የሱዳንን የተምታታ አቋም ያሳያል ብለዋል።

ሱዳን የእኔ ነው ያለችው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉዳይ ከድንበርም ሆነ ከህዳሴ ግድቡ ጋር
አይገናኝም ያሉት አምሳደር ዲና የኢትዮጵያ አቋም ከተመድ ምስረታና ከሊግ ኦፍኔሽን ጅማሮ ጀምሮ የሚታወቅና ለአለም ከፍተኛ ውለታ
ያለው መሆንና በእነዚህ ተቋማት ኢትዮጵያ የነበራትን ሚና ማስታወስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሱዳን ወዳጆቹም ሆኑ የጋራ ወዳጆቻችንማወቅ ያለባቸው

ሱዳን በተለይም የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና እያለች ይህንን ማድረጓ አስነዋሪ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሱዳን ቤንሻንጉል ጉሙዝ ለእኔ ነው እካሳለሁ ማለቷን አስመልክቶ ሰፊና ዝርዝር መልስ እያዘጋጀች መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ዲና ዛሬ መልሱ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 26 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

Source: Link to the Post

Leave a Reply