ሱዳን ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የጦር መሳሪያ ያዘች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ከኢትዮጵያ በሚያዋስናት ድንበር አቅራቢያ በርካታ የጦር መሳሪያዎች መያዟን አስታወቀች፡፡

የጦር መሳሪያዎቹ ከሰላ ግዛት አካባቢ የተያዙ ሲሆን፥ ቀላል እና ከባድ መሳሪያዎችም ይገኙበታል፡፡

የፀጥታ ኃይሎች የጦር መሳሪያዎችን ሰሞኑን ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ መያዝ መቻላቸውንም አስታውቀዋል፡፡

የሃገሪቱ ጦር በምስራቃዊ ሱዳን ሊኖር ይችላል ካለው የፀጥታ ስጋት ጋር ተያይዞ በአካባቢው ከፍተኛ ፍተሻና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ

The post ሱዳን ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የጦር መሳሪያ ያዘች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply