ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አሳሰቡ።                አሻራ ሚዲያ…

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አሳሰቡ። አሻራ ሚዲያ…

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አሳሰቡ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-30/4/13/ዓ.ም ባህር ዳር እንደሚታወቀው የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በምዕራብ አርማጭሆ በድጋሚ ጥቃት እየፈጸመ ሲፈጽም መቆየቱን አሻራ መዘገቡ ይታወቃል፡፡ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በአብርሀጅራ ወረዳ በስናር የእርሻ ልማት ካምፕ ውስጥ ጥቃት መፈጸሙን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፍጥጫ ሌላ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ችግር በውይይት እንድትፈታ ሳልቫ ኪር ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሱዳን ከድንበር ጋር ተይይዞ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ አሳስበዋል። ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል በመሆኑት ሻምስ ል ዲን ካባሺ የተመራ ልዕል በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚህ ወቅትም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የድንብር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ ነው ያሳሰቡት። በቀጠናው ምንም አይነት ጦርነት አያስፈልግም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሀገራቱ የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ መፍታት አለባቸው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply