ሱዳን ከኢጋድ ጋር ያለኝ ግንኙነት ተቋርጧል አለች፡፡

የምስረቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ኢጋድ በነገዉ ስብሰባ ላይ ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎን መጋበዙን ተከትሎ ግንኙነቴን አቋርጫለሁ ስትል ሱዳን አስታዉቃለች፡፡

የሱዳን መንግስት ኢጋድ የአገሪቱ ጠላት ከሆነዉ ቡድን ጋር ያለ እኔ ዕዉቅና ንግግር እንዲደረግ ለማመቻቸት በማሰብ ጥሪዉን አድርጓል ለዚህም ግንኙነቴን አቋርጫለሁ ብሏል፡፡

የሱዳን የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ ዉሳኔ የመጣዉ ኢጋድ ለነገዉ ስብሰባ ሱዳንን ከጋበዘ በኋላ የፈጥኖ ደራሽ ሃይል መሪ የሆኑትን ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎን ስብሰባዉን እንዲካፈሉ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ነዉ ብሏል፡፡

ይህ ግብዣ የሱዳንን ሉዓላዊነትን የጣሰ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ እና ቀጣናዊ የሆኑ የኢጋድ መተዳደሪያ ደንቦችንም ጭምር ያፈረሰ ነዉ ሲል ገልጾታል፡፡

በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሹ ሃይል መካከል በተነሳ ግጭት ምክንያት ሱዳን ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ በጦርነት እየታመሰች ትገኛለች፡፡

በተለያየ ጊዜ በሳዑዲ አረቢያ እና በአሜሪካ አሸማጋይነት የተሞከሩ የተኩስ አቁም ስምምነቶችም ጦርነቱን ማቆም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply