ሱዳን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግዛቴ አካል ነው ማለቷ የአገሪቱን አስነዋሪ ተግባር የሚገልፅ ነው ስትል ኢትዮጵያ ኮነነች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሱዳን መንግስት ከቤንሻንጉል…

ሱዳን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግዛቴ አካል ነው ማለቷ የአገሪቱን አስነዋሪ ተግባር የሚገልፅ ነው ስትል ኢትዮጵያ ኮነነች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሱዳን መንግስት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ጋር ተያይዞ እያራገበ ያለው ሀሳብ መሠረተ ቢስ ነው ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንዳሉት የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ድንበር መጣስና ዜጎችን ማፈናቀሉ ሳያንሰው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኔ ግዛቴ ነው ማለቱ አስነዋሪ ተግባር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሱዳንን መንግስት ወቅታዊ አካሄድ እንደምትኮንና የአለም አቀፋ ማህበረሰብም ካርቱም ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ትጠይቃለች ብለዋል አሞባሳደር ዲና።

ሱዳን በውጭ ጉዳይና በውሃ ሚኒስትሮቿ በኩል ከሰሞኑ እየነዛች ያለው የተሳሳተ መረጃም ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ሲገባና አርሶ አደሮችን ሲያፈናቅል የኢትዮጵያ መንግስት የሃይልን አማራጭን ያልተከተለው ችግሩ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት ስለነበረው እንደሆነም ተነስቷል።

ይሁን እንጂ ይህ አልበቃ ያለው የሱዳን መንግስት የቤንሻንጉል ክልል ግዛቴ ነው ማለቱ፣ እንዲሁም ግድቡን ከድንበር ጉዳይ ጋር እያገናኘ አሳሳች መረጃዎችን ማቅረቡን ቀጥሏል ብለዋል አምባሳደር ዲና።

ይህን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በአስነዋሪ ተግባር እንደሚፈርጀውና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ እንደሚያሳውቅ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ።

አባቱ መረቀ
ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply