
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታ ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀመንበር ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ላይ መሰማራቷ የሚያሳዝን ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሱዳን ምንም እንኳን የኢጋድ ሊቀመንበር ብትሆንም የኢትዮጵያን መሬት ወራ፣ ሰላማዊ ዜጎችን አፈናቅላ አሁንም ተጨማሪ መሬቶችን ለመውረር የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመች ነው ብሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሱዳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃ ሲሰማራ ከወረረችው የኢትዮጵያ መሬት ሰራዊቷን እንድታስወጣ እና ወደ ራሷ እንድትመለስ ጫና እንዲፈጥር በትዊትር ገጹ ላይ በማሰፈረው ፅኁፍ ጥሪ አቅርቧል።
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት የድንበር ልዩነቱን በግጭት መፍቻ መንገዶች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
The post ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post