ሱዳን 3,500 የውጭ ዜጎችን በቀድሞው ፓስፖርት እንዳይጠቀሙ ከለከለች፡፡ከሶስት አስርት አመታተት በላይ ሀገረ ሱዳንን በአምባገነን አገዛዝ የመሩትና ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት ከስ…

https://cdn4.telesco.pe/file/jBg8UdFw7PrWyAPNI2ZdYFgnr4RfyCF--zr6KXbAsncctuqkuZpte3tf_Xhu40qp49mEjQ7T5waJLn64Hj3osPjuyCq1DAvgWcHsZFnmrJ0MThP5G2FyvxsEEPpup50dD2a8AavG8zgwe_JINnT68Zy9hlHSj3oVM-98Cpih3wMkT7BinHN6UZbczs0vAYk_LT4mtmbjgXWB4xuVhxZAvWyixjREe3XOA3xk5VZsaLC1ssN_R4aXvenKoWEad5bb_jlGPfNB5zlbfAXlmT7J0HWGwIPoG5uQyRS6STkgnIQjMevgrXHwgVMqDHANVUpUyFteFfYe7oliatLi6Mov_w.jpg

ሱዳን 3,500 የውጭ ዜጎችን በቀድሞው ፓስፖርት እንዳይጠቀሙ ከለከለች፡፡

ከሶስት አስርት አመታተት በላይ ሀገረ ሱዳንን በአምባገነን አገዛዝ የመሩትና ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣል የተነሱት የቀድሞው የሱዳኑ መሪ ዑመር አል-በሽር እንደነበሩ ይታዎሳል፡፡

የአሁኑ የሱዳኑ ጊዚያዊ መንገግስት በዑመር አል-በሽር ዘመነ መንግስት ተከፍተው የነበሩ 3 ሺህ 500 ፓስፖርቶችን፤ የውጭ ሀገራት ዜጎች አሁን ላይ መጠቀም እንደማይችሉ ክልከላ ማድረጉ ነው የተሰማው፡፡

በካርቱም የውስጥ ዳጉይ ሚኒስቴር እንዳስታቀው፤ ክልከላው የተጣለበት ምክንያት በዚሁ ፓስፖርት በመጠቀም በርካታ ህገ ወጥ ድርጊቶች እንደሚፈጸሙና በተለይ ከደህነነት ጋር ግንኙነት ያለቸው መረጃዎች እንደሚወጡ በማረጋገጣችን ነው ብሏል፡፡

በምሳሌነትም ካረብ ሀገር ለሚገቡ ሰዎች በተለያ ከሶሪያ የሚመጡ ሰዎች ይህንን ፓስፖርት ለመግኘት እስከ 10 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሉ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡

ሶሪያዉያን ወደ ሱዳን መግባት ደግሞ በጣም እንደሚፈልጉ ገልጾ፤ በዚህም በሶሪያ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ150 ሺህ በላይ ሶሪያውያን በሱዳን እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በጅብሪል መሀመድ
ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply